የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አብዱል ራሁል ዛኪር

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አብዱል ራሁል ዛኪር ፣ ደግሞ በሌላ ስሙ ቃሪ ዘክር ተብሎ የሚታወቀው ለሀቃኒ አውታር የአጥፍቶ ጠፊ ድርጊቶች መሪ ነው እና በካቡል ፣ ታክሃር ፣ ኩንዱዝ ፣ እና በባግላን አፍጋኒስታን የሥራ አዛዥ ነው። ዛኪር መመሪያ በሚያጠቃልለው በትናንሽ የጦር መሳሪያዎች ፣ በከባድ የጦር መሳሪያዎች ፣ እና ቤት ውስጥ/በድብቅ የተሰሩ የሚፈነዱ መሳሪያዎች (IED) ግንባታ ኃላፊ ነው።

ዛኪር በልዋጭ በሰሜናዊ አፍጋኒስታን የቡድኑን ተጽዕኖና ድርጊት ለማስፋፋት የገንዘብ ዕርዳታ በመጠየቅ የሀቃኒ አውታር መሪ ስራጁዲን ሀቃኒን በ2008 ቀርቦታል ፣ እና የስራጁዲን ሚስጥረኛና የታመነ ወዳጅ ሆኖአል ። እርሱም በብዙዎቹ የሀቃኒ አውታር ከፍተኛ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች ታሳትፎአል እና በአካባቢ ወረዳ ደረጃ ባሉት አዛዦች የሚታቀዱት ሰፊ ጥቃቶች መፈጸም እንዳለባቸው ወይም እንደሌለባቸው አንዳንዶቹን የመጨረሻ ውሳኔዎች በማድረግ ላይ በከፊል ተጠያቂ ነው ። ከዛኪር የሥልጠና መርሃ ግብር በተመረጡ ሠራተኞች የተፈጸሙ ጥቃቶች የሚያጠቃልሉት በ2010 በሰሌሞና ቸፕማን የጥምር ኃይሎች ሠፈር ፣ በሰኔ 2011 በእንቴርኮንቲኔንታል ሆቴል ተፈጽሞ 11 ሲቪሎችንና ሁለት የአፍጋኒስታዊ ፖሊሶችን የገደለው ፣ በመስከረም 2011 በካቡል የአሜሪካ ኤምባሲ ተፈጽሞ ቢያንስ ስድስት ሕጻናትን ጨምሮ 16 አፍጋኒስታዊያንን የገደለው ነው።

የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በህዳር 5 ቀን 2012 በሥራ አፈጻጸም መመሪያ 13224 መሠረት አብዱል ራሁል ዛኪርን በልዩ ሁኔታ የተሰየመ የዓለም አቀፍ አሸባሪ አድርጎ ፈርጆታል።

የሀቃኒ አውታር ከ1980ዎቹ ከሶቪየት ኅብረት ጋር የተዋጋ በአፍጋኒስታን የጦር ሜዳ አዛዥ በነበረው ፣ በስራጁዲን ሀቃኒ የተመሰረተ ወታደራዊ ቡድን ነው። የሀቃኒ አውታር ከአፍጋኒስታን ታሊባንና ከአልቀይዳ ጋር በመተባበር በአፍጋኒስታን የታሊባን አገዛዝ መልሶ ለማቋቋም ይሻል። የሀቃኒ አውታር በዋናው መሠረቱ በሰሜን ዋዝርስታን፣ ፓኪስታን ነው ፣ እና ድንበር ዘለል ሥራዎቹን የሚሠረው ወደ ምሥራቅ አፍጋኒስታንና ካቡል ነው። ሀቃኒዎች በአፍጋኒስታን በጥምርና አፍጋኒስታን ኃይሎች ላይ የሚያነጣጥሩ እጅግ በጣም ገዳይ የሽፍታ ቡድን እንደሆኑ ይታወቃል።

የሀቃኒ አውታር በአፍጋኒስታን በአሜሪካና በጥምር ኃይሎች፣ እንዲሁም በአፍጋንስታን መንግሥትና በሲቪል ኢላማዎች ላይ በርካታ ትላልቅና ዋና አፈናዎችንና ጥቃቶችን አቅዶአል ፣ ፈጽሞአልም። ከቡድኑ አንዳንድ ከሁሉ እጅግ አስቃያሚ ጥቃቶች የሚያጠቃልሉት በካቡል በሰኔ 2011 በእንቴርኮንቲኔንታል ሆቴል ተፈጽሞ 11 ሲቪሎችንና ሁለት የአፍጋኒስታዊ ፖሊሶችን የገደለው ፣ በመስከረም 2011 በአፍጋኒስታን፣ በዋርዳክ አውራጃ 77 የአሜሪካ ወታደሮችን የገደለው የጭነት መኪና ቦምብ ፣ በመስከረም 2011 በካቡል በአሜሪካ ኤምባሲና በዓለም አቀፍ የዳህንነት መርጃ ኃይል (ISAF) ዋና ጽ/ቤቶ ላይ የተፈጸመ የ19 ሰዓት ጥቃት ፣ በሰኔ 2012 በForward Operating Base Salerno ላይ ተፈጽሞ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮችን ገድሎ ከ100 በላይ የቆሰለው የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት። በሰኔ 2012 በካቡል በእስፖዝማይ ሆቴል 14 ሲቪሎችን ጨምሮ ፣ ቢያንስ 18 አፍጋኒስታናዊያንን የገደለው የጦርነት ከበባ።

የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመስከረም 19 ቀን 2012 የሀቃኒን አውታር የውጭ አገር አሸባሪ ድርጅት አድርጎ ፈርጆታል።