የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አብዱል ሪህማን ያሲን

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

በኒውዮርክ የአለም ንግድ ማዕከል ላይ በ1993 ውስጥ የተፈፀመውን ጥቃት ራምዚ አህመድ የሱፍ በዋነኝነት ሲያቀነባብር ይህ አሸባሪ ቀጥተኛ እርዳታ አድርጎለታል፡፡ ዩሱፍና ያሲን ሙሉውን ፈንጅዎች የጫነ መኪና በመንዳት ወደ አለም ንግድ ማዕከል በማስገባት ስድሰት ሰዎች እንዲሞቱና ከአንድ ሺ በላይ ቁስለኛ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ የሲን እንዳይታሰር ከቦምብ ጥቃቱ በኋላ ወዲያውኑ ከአሜሪካ በመውጣት ሸሽቷል፡፡

ከቦንብ ጥቃቱ በኋላ፣ ያሲንን ጩምሮ በጥቃቱ የተሳተፉ ተጠርጣሪ አሸባሪዎች መሳተፋቸውን የሚያመለክቱና በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ያደረጉ መረጃዎችን የህግ አስከባሪዎች አግኝተዋል፡፡
ያሲን አሜሪካ ውስጥ ተወልዶ በ1960ዎቹ ውስጥ ወደ ኢራቅ በመሄድ በ1992 መጨረሻ ላይ ወደ አሜሪካ ተመልሷል፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት አለው፡፡

ከላይ በሥም የተጠቀስው ግለሰብ በሚከተሉት ክሶች ተወንጅሏል:

በእሳት ወይም በፍንዳታ ጉዳት ማድረስ፣ በአሜሪካ ንብረቶች ላይ በእሳት ወይም በፍንዳታ ጉዳት ማድረስ፣ በአገር ውስጥ ንግድ ላይ ፈንጅ ማጓጓዝ፣ የሞተር ተሽከርካሪዎችን ማቃጠል፣

በአሜሪካዊያን ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ ማሴር፣ መርዳትና መፈፀም የድርጊቱ ውጤት ሞት ሲሆን የሞት ቅጣት ወይም የእድሜ ልክ እስራት ፍርድ፣ በስራው ላይ ያለ የፌደራል ኦፊሰር ላይ አካላዊ ጥቃትና ጉንተላ ማድረስና፣ ግዳይ የጦር መሳሪያን በመጠቀም የአመፅ ወንጀል መፈፀም

የ-----ተጨማሪ ፎቶ

አብዱል ሪህማን ያሲን