የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አብዱል ዋሊ

እስከ $3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አቡዱል ዋሊ ከ Tehrik-e-Taliban (TTP) Pakistan ጋር ግኑኝነት ያለው የ Jamaat ul-Ahrar (JuA) መሪ ነው። እርሱ ከአፍጋኒስታን ናንጋርሃር እና ኩናር ክፍለ ሀገሮች ውስጥ እንደሚሠራ ይነገራል።

በዋሊ አመራር ሥር፣ በፑንጃብ ክፍለ አገር JuA እጅግ በጣም ተዋጊ ከሆኑት TTP መረቦች አንዱ ሆኖ በመላው ፓኪስታን በርካታ የቦምብ ጥቃቶችንና ሌሎች ጥቃቶችን እንዳካሄደ ተናገሮአል።

በመጋቢት 2016፣ JuA በህዝብ መናፈሻ በላሆር ፓኪስታን 75 ሰዎችን ገድሎ 340 ሰዎችን ያቆሰለውን የቦምብ ጥቃቶችን አካሄዶአል።

በነሀሴ 2015፣ የፑንጃቢ የአገር ውስጥ ሚንስቴር ሹጃ ካንዛዳንና ከደጋፊዎች 18ቱን ለገደለው የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች ኃላፊነት ወስዶአል።

ዋሊ ካሊድ ኮርሳኒ በመባልም ተብሎ ይታወቃል። እርሱ የተወለደው በሞ ሀመንድ አጀንሲ፣ በፓኪስታን ነበረ፣ እና ዕድሜው በ30ዎቹ መጨራሻ አካባቢ እንደሆነ ይታመናል። እርሱም የቀድሞ ጋዜጠኛ እና ባለቅኔ ነው እና በካራቺ በርካታ ማድራሶችን አጥንቶአል።

የተጨማሪ ፎቶ

አብዱል ዋሊ