የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አብዱል ሳቡር

እስከ $3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አብዱል ሳቡር Hezb-e Islami Gulbuddin (HIG) ጋር የተያያዘ የፈንጂ ባለሞያ ነው።

ሳቡር እ ኤ አ በግንቦት 16 ቀን 2013 በካቡል፣ አፍጋኒስታን የአሜሪካን የጦር መሳሪያ የጫነ መኪና ደምስሶ ሁለት ወታደሮችንና አራት የአሜሪካ የሲቪል ኮንትራክቴሮችን ፣ ሁለት ልጆችን ጨምሮ – ስምንት አፍጋኒስታዊያንን ለገደለውና – ቢያንስ 37 ሌሎችን ላቆሰለው እቤት ውስጥ ለተሰራው (SVBIED) የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት ተጠያቂ ነው።

ሳቡርና የከፍተኛ ፈንጂዎች ባለሞያ አብዱላህ ኖውባሃር በካቡል ዓለም አቀፍ አየር ጣቢያ የውጭ አገር ሠራተኞችን ጭኖ በሚጓዘው አውቶቡስ ላይ ፈንድቶ ከአሥር በላይ ሰዎች በተገደሉበት ለመስከረም 18 ቀን 2012 ዓ ም የSVBIED ጥቃት ቁልፍ ተሳታፊ ናቸው።