የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አብደራውፍ ቤን ሃቢብ ጅዴይ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አብደራውፍ ጄዴይ፣ አለበለዚያም ፋሩቅ አል ቱኒዚ፣ በጣም በናሩ በወጡ የፅንፈኝነት አቋሞቹ ይታወቃል፡፡ ከአልቃኢዳ ዘመቻዎች ጋር በቅርብ ቁርኝት ያለው ሆኖ በጠለፋ/የሽብር ዘመቻዎች እቅድ ማውጣት ላይ ተሳታፊ ነበር፡፡ ጃዴይ የቱኒዚያዊ አሸባሪው ፋኪር ቦሶራ ጋር ተባባሪ ሲሆን ምናልባትም ከዚህ በፊት ሁለቱም አብረው ተጉዘዋል፡፡

ጅዴይ በ1991 አገሩን ቱኒዚያን ለቆ ወደ ካናዳ፣ ሞንትሪያል በመሄድ 1995 ውስጥ የካናዳን ዜግነት አግኝቷል፡፡ ጅዴይ ካናዳ ውስጥ በሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ ባዮሎጂን ያጠና ሲሆን በሞንትሪያል ወደ አሱና መስጊድ ይሄድ ነበር፡፡

ጅዴይ በ1993 ካናዳን በመልቀቅ እስከ 2000 ድረስ አፍጋኒስታን ውስጥ የውጊያ ስልጣናና ልምድ አግኝቷል፡፡ ከአፍጋን የሰሜን ህብረት ጋር በተደረጉ ውጊያዎች በመሳተፍ በጅሃድ ሰማእት ለመሆን ያለውን ፍላጎቱን የገለፀበት ደብዳቤ ፅፏል፡፡ ጅዴይ በዚህ ወቅት በአልቃኢዳ መሪ ቤት ውስጥ በ2001 በተገኘ በጣም ታዋቂ በሆነ የሰማእትነት ቪዲዮ ውስጥ ታይቷል፡፡

በ2001 ወደ ሞንትሪያል ከተመለሰ በኋላ የጅሃድ አባል እንዴት መሆን እንደሚችል ከአክራሪዎች ጋር ከተወያየ በኋላ ጅዴይ ካናዳን ለቆ ወጣ፡፡ ባለስልጣናት አሁንም ጅዴይ ወደ ካናዳ ወይም ወደ አሜሪካ በመግባት በሽብር ጥቃት ውስጥ ለመሳተፍ ሊሞክር ይችላል የሚል ስጋት አላቸው፡፡

የ-----ተጨማሪ ፎቶ

የ-----ተጨማሪ አብደራውፍ ቤን ሃቢብ ጅዴይ
የ-----ተጨማሪ አብደራውፍ ቤን ሃቢብ ጅዴይ