የሚፈለጉ
ፍትህ የሚያመጣ መረጃ…

አብዴልበሲት፣አልሀጅ፣አልሀሰን ሀጅ ሃማድ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

በጥር 1, 2008፣ የዩስ ኤስ ዜጋና የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት(USAID) ሠራተኛ እና ሱዳናዊ ሾፌሩ አብዴልረሃማን አባስ ረህማን፣በካርቱም ሱዳን ከአዲስ ዓመት ዋዜማ በዓል ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ተተኩሶባቸው ሞተዋል። ዕድሜው 33 ዓመት የነበረው ግራንቪል፣በዲሞክራሲና መንግሥት አገዛዝ መርኃ ግብር እየሠራ ነበረ። ዕድሜው 39 ዓመት የነበረው አባስ ለደርፉር የአደጋ ዕርዳታ ምላሽ ቡድን አባል ሆኖ ነበረ በUSAID በ2004 የተቀጠረው። ለጥቃቱ ሁለት ቡድኖች ኃላፊነቱን ወስደዋል። አንሳር አል- ታውሂድ (በአንድ አምላክ የሚያምኑትን ደጋፊዎች) እና በሁለት አባይ ወንዞች መካከል ባለው ምድር ያለ አልቃይዳ (AQTN)።

የሱዳን ህግ አካል በግድያ በመሳተፋቸው በአምስት ሰዎች ላይ ክስ መስርቶ ፈርዶባቸዋል። አብዴልራውፍ አቡ ዛይድ መሀመድ ሀምዛ፣ መሀመድ መካዊ እብራሂም መሀመድ፣አብዴልበሲት አልሃጅ አልሃሳን ሀጅ ሀመድ፣እና መሀመድ ኦስማን ዩሲፍ መሀመድ በመሰቀል በሞት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው ነገር ግን ከፍርዱ ብያኔ በኋላ ከአንድ ዓመት በኋላ ከእስር ቤት አመለጡ። መሀመድ በግንቦት2011 በሶማሊያ እንደሞተ ተዘግቦአል። አብዴልራውፍ እንደገና በሱዳን ባለሥልጣን ተማርኮአል። መካዊና አብዴልበሲት እንዳመለጡ ቀርተዋል።

አብዴልበሲት በግድያው ሁለተኛ ተኳሽ ነበረ። እርሱም በሰኔ 11, 2010 በካርቱም ከሚገኘው ከኮባር እስር ቤት አምልጦ አሁን በሶማሊያ ነው ያለው።