የቅርብ ጊዜ ዜና

ካሲም አል-ሪሚ

እስከ $10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ቃሲም አል-ሪሚ፣ ለአልቃኢዳ መሪ አይማን አልዘዋሃሪ ታማኝነቱን ካረጋገጠ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. በሰኔ 2015 ውስጥ የAQAP እምር ሆኖ ተሰይሞአል፣ እና በዩናይትድ ስቴትስ ላይ እንደገና ጥቃቶች እንዲፈፅሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡ አል-ሪሚ በ1990ዎቹ በአፍጋኒስታን የአልቃኢዳ ካምፕ አሸባሪዎችን አሠለጠነ፣ እና ከዚያም ወደ የመን ተመልሶ የAQAP ወታደራዊ አዛዥ ሆነ፡፡ በ2005 በየመን የአሜሪካን አምባሳደር ለመግደል በማሴሩ የአምስት ዓመት እስራት ተፈርዶበታል፣ እና በ2006 አመለጠ፡፡ በመስከረም 2008 በሰናአ በአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ተከስቶ 10 የየመን ጠባቂዎችን፣ አራት ሰላማዊ ሰዎችን እና ስድስት አሸባሪዎችን ከገደለው ጥቃት ጋር አል-ሪሚ ተያይዞአል፡፡ ወደ አሜሪካ በሚጓዘው አውሮፕላን ላይ ከታህሳስ 2009 “የውስጥ ልብስ ቦምብ አፈንጂ” ከአጥፍቶ ማጥፋት ሙከራ ኡማር ፋሩክ አብዱልሙታላብ ጋር አል-ሪሚ ተያይዞአል፡፡ በየመን የአቢያን ግዛት የአልቃኢዳን ማሰልጠኛ ካምፕ በማንቀሳቀሱ እ.ኤ.አ በ2009፣ የየመን መንግሥት ከሶታል ፡፡

(ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

ካሊድ ሳኢድ አል-ባተርፊ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ካሊድ አል-ባታርፊ በየመን ሃድረማውት ግዛት የAQAP ከፍተኛ አባልና የቀድሞው የ AQAP የሹራ ምክር ቤት አባል ነው፡፡ በ1999፣ በአልቃኢዳ የአል-ፋሩቅ ካምፕ ውስጥ አሰልጣኝ፣ ወደ ነበረበት ወደ አፍጋኒስታን ተጓዘ፡፡ እርሱ እ.ኤ.አ. በ 2001፣ ከታሊባንን ጋር ከአሜሪካ ኃይሎች እና ከሰሜን ማህበር ጋር ተዋግቷል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2010፣ አል-ባትርፊ AQAPን በየመን ተቀላቅሎአል፣ የየመን አቢያን ግዛት በመውረር የAQAP ወታደሮችን መርቶአል፣ እና፣ የአቢያን የAQAP እምር የሚል ስም ተሰጠው፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2016 በዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ጥቃት የ AQAP መሪ ናሲር አል – ውሃይሽይ ከሞተ በኋላ፣ አልቃይዳ የአሜሪካን ኢኮኖሚ እንደሚያጠፋ እና ሌሎች የአሜሪካን ጥቅሞችን እንደሚያጠቃ የማስጠንቀቂያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

(ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

አብዱላህ አህመድ አብዱላህ

እስከ $10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

p>አብዱላህ የአልቃይዳ አንጋፋ መሪ እና “የመጅሊስ አል- ሹራ” ፣ የአልቃይዳ አመራር ምክር ቤት አባል ነው ፡፡አብዱላህ ልምድ ያለው የአልቃይዳ የገንዘብ ሹም ፣ የሚያመቻች፣ እና የድርጊት አቃጅ ነው፡፡

አብዱላህ፣ በደሬሳለም፣ ታንዛኒያ እና በናይሮቢ፣ ኬንያ፣ በነሀሴ 7 ቀን 1998 ፣ በአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ለደረሱት የቦምብ ጥቃቶች በነበረው ሚና፣ በታህሳስ 1998 በፌዴራል ጠቅላይ የፍርድ ጁሪ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ ጥቃቶቹ 224 ሲቪሎችን ገድሎ ከ5,000 በላይ የሆኑትን ሌሎችን አቁስሎአል፡፡

በ1990ዎቹ፣ አብዱላህ ለአልቃይዳ ተዋጊዎች እንዲሁም በ Operation Restore Hope ወቅት ከአሜሪካ የጦር ሃይሎች ጋር ለተዋጉት ለሶማሊያ የጎሳ ሰዎች የውትድርና ሥልጠና ሰጥቶአል፡፡ እርሱም ከ1996-1998፣ በአፍጋኒስታን ፣ የአልቃይዳ የሥልጠና ካምፖችን አካሄዶአል፡፡

(ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

ሰይፍ አል አደል

እስከ $10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አል – አድል የአልቃይዳ አንጋፋ መሪና “የመጅሊስ አል- ሹራ” ፣ የአልቃይዳ አመራር ምክር ቤት አባል ነው ፡፡አል – አድል የአልቃይዳን ተወታደራዊ ኮሚቴን ይመራል፡፡

አል – አድል፣ በደሬሳለም፣ ታንዛኒያ እና በናይሮቢ፣ ኬንያ፣ በነሀሴ 7 ቀን 1998 ፣ በአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ ለደረሱት የቦምብ ጥቃቶች በነበረው ሚና፣ በታህሳስ 1998 በፌዴራል ጠቅላይ የፍርድ ጁሪ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ ጥቃቶቹ 224 ሲቪሎችን ገድሎ ከ5,000 በላይ የሆኑትን ሌሎችን አቁስሎአል፡፡

እርሱም ከግብጽ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር የግድያ ሙከራ በኋላ በ1987 ከሌሎች የጸረ መንግሥት ተዋጊዎች ጋር እስከታሰረ ድረስ በግብጽ የልዩ ሃይሎች ውስጥ ሌተናንት ኮሎኔል ነበረ

በ1990 መጀመሪያ፣ አል አድል እና ሌላ የአልቃይዳ ተዋጊዎች፣ አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታንና ሱዳን፣ የግብጽ እስላማዊ ጂሃድ ጭምር ለአልቃይዳና ከርሱ ጋር ተዛማጅ ለሆኑ ቡድኖች፣ በተለያዩ አገሮች የውትድርናና የእንቴልጄንስ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

(ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

አብዱል ዋሊ

እስከ $3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

አቡዱል ዋሊ ከ Tehrik-e-Taliban (TTP) Pakistan ጋር ግኑኝነት ያለው የ Jamaat ul-Ahrar (JuA) መሪ ነው። እርሱ ከአፍጋኒስታን ናንጋርሃር እና ኩናር ክፍለ ሀገሮች ውስጥ እንደሚሠራ ይነገራል።

በዋሊ አመራር ሥር፣ በፑንጃብ ክፍለ አገር JuA እጅግ በጣም ተዋጊ ከሆኑት TTP መረቦች አንዱ ሆኖ በመላው ፓኪስታን በርካታ የቦምብ ጥቃቶችንና ሌሎች ጥቃቶችን እንዳካሄደ ተናገሮአል።

በመጋቢት 2016፣ JuA በህዝብ መናፈሻ በላሆር ፓኪስታን 75 ሰዎችን ገድሎ 340 ሰዎችን ያቆሰለውን የቦምብ ጥቃቶችን አካሄዶአል።

(ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

መንገል ባግ

እስከ $3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

መንገል ባግ፣ ከTehrik-e-Taliban Pakistan (TTP) ጋር ግኑኝነት ላለው ለ Lashkar-e-Islam መሪ ነው። ቡድኑ ገቢ የሚያገኛው አደንዣዥ ዕጽን በማመላለስ፣ በኮንትሮባንድ፣ በአፈና፣ የNATO አጃቢ መኪናዎችን በመበርበር፣ በፓኪስታንና በአፍጋኒስታን መተላለፊያ ንግድ ላይ ቀረጥ በመቅረጥ ነው።

ባግ Lashkar-e-Islamን ከ2006 ጀምሮ መርቶአል እና እርሱ በሚቆ ጣጠራቸው፣ በተላይ በአፍጋኒስታን፣ናንጋርሃር ክፍለ ሃገር በምስራቅ አፍጋኒስታንና በምዕራብ ፓኪስታን አካባቢዎች አክራሪ ዲኦባንዲ የእስልምና ቅጂ ህገወጥ የገቢ ምንጮችን ለመከላከል በመደበኛ ሁኔታ ወዳጅነቶችን ቀይሮአል።

በካይቤር አጀንሲ፣ በፓኪስታን የተወለደው፣ ዕድሜው በመካከለኛ አርባዎቹ መካከል እንደሆነ ይታመናል።ባግ የአፍሪዲ ጎሳ አባል ነው። እርሱ ለበርካታ ዓመታት በማድራሳ አጥንቶአል እና በኋላ በአፍጋኒስታን ከወታደራዊ ቡድኖች ጋር ተዋግቶአል።

(ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

አህላም አህመድ አል- ታሚሚ

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ደግሞ “ ካህልቲ” እና “ ሃላቲ” ተብላ የምትጠራው ዮርዳኖሳዊ ዜጋ የሆነችው፣ አህላም አህመድ አል- ታሚሚ ለሃማስ የምትሰራ አሸባሪ በመሆኗ ተፈርዶባታል።

እ ኤ አ በነሀሴ 9 ቀን 2001 ዓ ም ፣ አል- ታሚሚ ቦምብና የሃማስ አጥፎ ጠፊ ቦምብ አፈንጂን ህዝብ ወደ ሞላበት ወደ ኢየሩሳሌም ስባሮ ፕዜሪያ አጓጉዞለች። ቦምብ አፈንጂው ፈንጂውን አፈንድቶ፣ ሰባት ልጆችን ጨምሮ፣ 15 ሰዎችን ገድሎአል። በጥቃቱ ሁለት የአሜሪካ ዜጎችም ተገድለዋል – እርጉዝ የነበረች ዕድሜዋ 31 ዓመት የነበረ ከኒው ጄርሲ መምህርት የነበረች ጁዲት ሾሸና ግሪንባውም፣ እና ዕድሜዋ 15 ዓመት የነበረው ማልካ ቻና ሮዝ ተገድለዋል። አራት አሜሪካዊያንን ጨምሮ ከ20 በላይ ሌሎች ሰዎች ቆስለዋል። ለቦምቡ ጥቃት ሃማስ ኃላፊነቱን ወስዶአል።

እ ኤ አ በ2003 ፣ አል- ታሚሚ በእስራኤል ፍርድ ቤት በጥቃቱ በመሳተፏ ጥፋተኛ መሆኑን አመነ እና ቦምብ አፈንጂውን በማገዙ ለ16 የህይወት ዘመን እስረት ተፈርዶበታል። እርስዋም በእስራኤልና በሀማስ መካከል በተደረገው የእስረኞች ልውውጥ በጥቅምት 2011 ተለቃለች። በመጋቢት 14 ቀን፣ የአሜሪካ የፍትህ ሚንስቴር የወንጀል ክስ አጋልጦ አል- ታሚሚ እንድትታሰር ትዕዛዝ አወጣ እና በአሜሪካ ህግ መሰረት “ ከአሜሪካ ውጭ፣ ሞት ያስከተለውን በጅምላ አጥፊ የሆነ የጦር መሳሪያ ለመጠቀም በማሴሯ“ ክስ ተመሰርቶባታል። ” ኤፍ ቢ አይ ደግሞ አል- ታሚሚን በእጅጉ ከሚፈለጉ አሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ጨምሮአታል እና “ መሳሪያ የታጠቀችና አደገኛ ” እንደሆነች ይገነዘባታል።

(ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

ተላል ሃሚያ (Talal Hamiyah)

እስከ $7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ተላል ሃሚያ የተደራጁ እስር ቤቶችን የሚጠብቀው የሂዞቦላ የውጭ ዳህንነት ድርጅት (External Security Organization (ESO)) ኃላፊ ነው። ESO ከሊባኖስ ውጭ የሽብርተኝነት ጥቃቶችን ለማቀድ፣ ለማስተባበር ፣ እና ለማስፈጸም ኃላፊነት ያለበት የሂዞቦላ አካል ነው። ጥቃቶቹ በዋናኛው ያነጣጠሩት እስራኤላዊያንና አሜሪካዊያንን ነው።

የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር በሥራ መመሪያ 13224 መሰረት ተላል ሃሚያን በመስከረም 13 ቀን 2012 በተለየ ሁኔታ የተሰየመ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪ አድርጎ (Designated Global Terrorist (SDGT)) ፈርጆታል።

(ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

ፉአድ ሹክር (Fuad Shukr)

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ፉአድ ሹክር በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ለሂዝቦላ ጠቅላይ ጸሐፊ ለሆነው ለሃሰን ናስራላ የረጅም ጊዜ አንጋፋ አማካሪ ነው። ሹክር በደቡብ ሊባኖስ የህዝቦላ ኃይሎች የወታደራዊ አሻዥ የሆነ አንጋፋ የሂዝቦላ ወታደር ነው። እርሱ የህዝቦላ ከሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ አካል፣ የጂሃድ ምክር ቤት አገልጋይ ነው።

ሹክር ለህዝቦላና በሂዝቦላ ፈንታ የሚያደርጋቸው ድርጊቶች ከ30 ዓመታት በላይ ዘልቀዋል። እርሱም በቅርቡ ለሞተው ለህዝቦላ አዛዥ ለሆነው ለእማድ ሙግኒያህ የቅርብ ባልደረባ ነበረ። ሹክር በእ ኤ አ በጥቅምት 23 ቀን 1983 ዓ ም፣በቤሩት፣ሊባኖስ በአሜሪካ የባህር ኃይል ሠፈሮች ጥቃት አድርሶ 241 የአሜሪካ አገልግሎት ሰጭዎችን የገደለውን ቦምብ በማቀድና በማስፈጸም ማዕከላዊ ሚና ተጫውቶአል።

(ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

ሙሀመድ አል- ጃውላኒ (Muhammad al-Jawlani)

እስከ $10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ደግሞ አቡ ሙሀመድ አል – ጎላኒ ተብሎ የሚታወቀው ሙሀመድ አል – ጃውላኒ፣ ደግሞ ሙሀመድ አል- ጁላኒ ተብሎ የሚታወቀው፣ የአልቀይዳ የሶሪያ ቅርንጫፍ የአል- ኑስራህ (the al-Nusrah Front (ANF)) ግምባር የአሸባሪ ድርጅት አንጋፋ መሪ ነው። እ ኤ አ በሚያዚያ 2013፣ አል- ጃውላኒ ታማኝነቱን ለአልቃይዳና ለመሪው አይማን አል- ዛዋሪ ሰጠ። በሀምሌ 16፣ በእንቴርኔት ቪዲዮ አል- ጃውላኒ አልቃይዳንና አል- ዛዋሪን አመስግኖአል እና ANF ስሙን ወደ ጃብሃት ፋት አል ሻም (“የሌቫንት ግምባር አሸናፊነት”) እንደ ቀየረ ተናግሮአል። በአል- ጃውላኒ አመራር፣ANF ዘወትር ሲቪሎችን በማነጣጠር በመላው ሶሪያ በርካታ የአሸባሪነት ጥቃቶችን አካሄዶአል። በሚያዚያ 2015፣ ANF በሶሪያ ፍተሻ ጣቢያ በግምት 300 የኩርድ ሲቪሎችን አግቶ በኋላ እንደለቀቃቸው ተነግሮአል። በሰኔ 2015፣ ANF በሶሪያ፣ በዱሬዝ መንደር በቃልብ ላውዜህ 20 ኗሪዎችን ገድዬአለሁ ብሎ ኃላፊነት ወስዶአል። (ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

ኢዮኤል ዌስሌ ሽራምን በመግዳል

ታይዝ፣ የመን | እ ኤ አ መጋቢት 18 ቀን 2012።

ኤ አ አ በመጋቢት 18 ቀን 2012፣ ዕድሜው 29 የሆነ ሽራም በታይዝ፣ የመን ወደ ሥራ ሲሄድ ሲሄድ በመንገድ ላይ ወደ መኪናው ተጠግቶ በሞቶር ብስክሌት ላይ ሆኖ በተኮሰበት በጠብመንጃ አንጋቢ ተገድሎአል። በሞቱ ጊዜ፣ ሽራም በ International Training and Development Center አስተዳዳሪና የእንግሊዝኛ አስተማሪ ሆኖ ይሰራ ነበረ። እርሱም በየመን ከምስቱና ከሁለት ለጋ ልጆቹ ጋር ይኖር ነበረ። ከጥቃቱ ጥቂት ቀናት በኋላ፣ አሸባሪው ድርጅት የአረቡ ባህረ ሰላጤ አልቃይዳ al-Qaida in the Arabian Peninsula (AQAP) ለግድያው ኃላፊነቱን ወስዶአል። የወሮታ ለፍትህ (Rewards for Justice program) መርኃ ግብር የአሜሪካ ዜጋ የሆነውን ኢዮኤል ሽራምን የገደሉትን፣ በግድያው ላይ ያሴሩትን፣ ወይም ያገዙትን ሰዎች ለማስያዝ ወይም ለማስፈረድ የሚመረውን መረጃ ለሚያቃብል እስከ $5 ሚሊዮን የሚደርስ ሽልማት እየሰጠ ነው። (ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

አቡ ባክር አል – ባግዳዲ (Abu Bakr al-Baghdadi)

እስከ $25 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

ደግሞ አቡዱሃ በመባል የሚታወቀውአቡ ባክር አል- ባግዳዲ፣ ደግሞ “ አዋድ እብራሂም አ- አልባድሪ በመባል የሚታወቀው ፣ የአሸባሪ ድርጅት የኢራቅና ሌቫንት እስላማዊ መንግስት (ISIL) አንጋፋ መሪ ነው። እርሱ የሚገኝበትን ቦታ ፣ እርሱን ለማስያዝ፣ ወይም ለማስፈረድ የሚያደርሰውን መረጃ ለሚያቃብል ሰው የውጭ አገር ሚንስቴር $10 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ ለመስጠት በ2011 ካሳወቀበት ጊዜ ጀምሮ አል- ባግዳዲ የሚያካሄደው ጥቃት በጣም ጨምሮአል ። በሰኔ 2014፣ ISIL (ዳኤሽ በመባል የሚታወቀው)የሶሪያንና የኢራቅን ከፊል ተቆጣጥሮአል እና የእስላማዊ ካሊ ፌት ማቋቋሙን፣ እና አል- ባግዳዲን ካልፈው እንዳደረገ በአዋጅ አሳውቆአል። በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ ISIL በመላው ዓለም የጂሃድስት ቡድኖችንና አክራሪ የተደረጉ ግለሰቦችን ታማኝነት አግኝቶአል፣ እና በአሜሪካ ላይ ጥቃቶችን አነሳስቶአል። (ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

ጉልሙሮድ ካሊሞቭን (Gulmurod Khalimov)

እስከ $3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

የቀድሞ የታጅክስታን የልዩ ኦፕሬሽኖች ኮሎኔል፣ የፖሊስ አዛዥ ፣ እና ወታደራዊ ጠብመንጃ አንጋች ጉልሙሮድ ካሊሞቭ የ የእራቅና ሌቫንት እስላማዊ መንግሥት (ISIL) አባልና መልማይ ነው። እርሱም በታጅክስታን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ልዩ የሽምቅ ውጊያ ክፍል አዛዥ ነበረ። ካሊሞቭ ለISIL መዋጋቱን በሚያረጋግጥ በፕሮፖጋንዳ ቪዲዮ ታይቶአል እና በአሜሪካኖች ላይ የአመጽ ተግባሮች እንዲነሳሱ ባይፈ ጥሪ አድርጎአል። (ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

አቡ – ሙሀመድ አል – ሽማሊ (Abu-Muhammad al-Shimali)

እስከ $5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ ወሮታ

በተሻለ ሁኔታ አቡ – ሙሀመድ አል – ሽማሊ በመባል የሚታወቀው ታራድ አል-ጀርባ ቀድሞ አል-ቃይዳ በኢራቅ ተብሎ ለሚታወቀው የኢራቅና የሌቫንት እስላማዊ መንግሥት (Islamic State of Iraq and the Levant (ISIL) ከ2005 ጀምሮ አንጋፋ የድንበር ኃላፊ ነው። እርሱ አሁን በISIL የእምግሬሽንና ሎጂስትካዊ ኮሚቴ ቁልፍ ባለሥልጣን ነው፣ እና የውጭ አገር አሸባሪ ተዋጊዎችን በዋናኛው በጋዚያንቴፕ፣ ቱርክ፣ እና በሶሪያ በISIL ቁጥጥር ሥር ወዳለችው ወደ ጀረቡሉስ ከተማ ድንበር ጉዞ በማመቻቸት ኃላፊ ነው። የእምግሬሽንና ሎጂስትካዊ ኮሚቴና አል-ሽማሊ (ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)

የኢራቅና የሌቫንት እስላማዊ መንግሥትን (the Islamic State of Iraq and the Levant (ISIL)) ለመጥቀም የሚጓዙትን የዘይትና የጥንት ዘመን ዕቃዎችን በደንብ ለማቋረጥ የሚመረውን መረጃ ለሚያቃብል—

የወሮታ ለፍትህ (Rewards for Justice program) መርኅ ግብር በአረብኛ ምህጸረ ቃል ዳኤሽ (DAESH) ተብሎ በሚታወቀው በ ፣ ለአሻባሪ ቡድን ፣ እስላማዊ መንግሥት (ISIL) ፣ የዘይትና የጥንት ዘመን ዕቃዎች ንግድ እና /ወይም ሽያጭ በደንብ ለማቋረጥ የሚመረውን መረጃ ለሚያቃብል እስከ $5 ሚሊዮን የሚደርስ ሽልማት እየሰጠ ነው። ISIL የመሳሰሉ አሻባሪ ቡድኖች ድርጊቶቻቸውን ለመቀጠልና ጥቃቶችን ለማካሄድ ገንዘብና ድጋፍ በሚሰጡት ላይ ይመካሉ። የISIL ህገወጥ የዘይት ሥራዎችና ከሶሪያና ከኢራቅ የተዘረፉ የአርኪዮሎጂ እቃዎች ንግድ ቁልፍ የገቢ ምንጮች ናቸው፣ እነዚህም (ራምዚ አህመድ ዩሴፍ »)