ወሮታ ለፍትሕ ስለ አይሲስ-ኬ መሪ አል-ሙሃጅር መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በሰኔ 2012፣ የአይሲስ ማዕከላዊ አመራር አል-ሙሃጅርን፣ በሌላ ስሙ ሳናኡላህ ጋፋሪ፣ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሽብርተኛ ተብሎ የተሰየመው አይሲስ-ኬ መሪ አድርጎ ሾሞታል፡፡ ሹመቱን በማስመልከት አይሲስ ባወጣው መግለጫ አል-ሙሃጅር ልምድ ያለው ወታደራዊ መሪ እና በካቡል ከተማ ከአይሲስ-ኬ “የከተማ አንበሶች” መካከል አንዱ ነው ብሏል፤ ይህ ግለሰብ በሽምቅ ውጊያዎች እና የአጥፍቶ ጥፊ እና ሌሎች ውስብሰብ ጥቃቶችን በማቀድ ተሳትፏል፡፡ በ1986 ዓ.ም. በአፍጋኒስታን የተወለደው ይህ ግሰለብ በመላው አፍጋኒስታን በአይሲስ-ኬ የተካሄዱ ኦፕሬሽኖችን እና ለእነርሱም ገንዘብ በማመቻቸት በኃላፊነት የሚጠየቅ ነው፡፡