ወሮታ ለፍትሕ የሒዝባላ የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎችን ለማቃወስ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሃሲብ ሙሀመድ ሃድዋን፣ በሌላ ስሙ ሃጂ ዛያን፣ ከፍተኛ የሂዝባላህ ዋና ጸሐፊ ነው፡፡ የሂዝባላህ ዋና ጸሐፊ የሃሰን ናስራላህ የቅርብ የበታች ኃላፊ ሲሆን፣ ከሊባኖስ ውጪ ካሉ ረጂዎች እና ነጋዴዎች ገንዘብ የማሰባሰብ ኃላፊነት አለው፡፡ በሂዝባላ ያለው ሥራ እና ኃላፊነት አካል በሆነ መልኩ ሃድዋን እና የቢሮ ሥራ አስኪያጁ አሊ ሳህዒር ወደ ሊባኖስ ገንዘብ ለማሰተላለፍ ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሲስተም ይጠቀማል፤ ነገር ግን ገንዘብ ያሰባሰበበትን ትክክለኛ ምክንያት ማለትም የድርጅቱን የሽበር እንቅስቃሴ የመደገፍ ዓላመውን ይደብቃል፡፡
በመስከረም 07 ቀን 2014 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ሃድዋንን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሃድዋን ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሃድዋን ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡