ወሮታ ለፍትሕ በነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በካቡል ዓለም ዓቃፍ አየር ማረፊያ፣ አፍጋነስታን ስለተፈጸመው ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች መንግሥታት ዜጎቻቸውን እና ሌሎች ተጋላጭ የአፍጋኒስታን ዜጎችን ከአገሪቱ ለማውጣት ሰፊ ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት አንድ አጥፍቶ ጠፊ በአውሮፕላን ማረፊያው ላይ ጥቃት ፈጸመ፡፡ በዚህ ጥቃት ጥረቱን ሲያግዙ የነበሩ 13 የአሜሪካ ወታደሮችን ጨምሮ ቢያንስ 185 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ በጥቃቱ 18 የአሜሪካ የጦር ኃይል አባላትን ጨምሮ ከ150 ሰዎች በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሽብርተኛ የሆነው አይሲስ-ኬ ለዚህ ጥት ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡