የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ይፋዊ ዌብሳይት

አሊ ሳዴ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ የሒዝባላ የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎችን ለማቃወስ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አሊ ሳዴ በጊኒ የሚንቀሳቀስ የሂዝባላህ ገንዘብ አቅራቢ ወይም ፋይናንሰር ነው፡፡ ሳዴ ከጊኒ ወደ ሂዝባላ የሚደረገውን ገንዘብ ማስተላለፍ ያካሂዳል፤ ይህም ማለት በጊጂ እና ሊባኖስ ከሚገኙ የሂዝባላህ ወኪሎች ገንዘብ ያስተላልፋል፡፡

በቅርቡ በ2012 ዓ.ም. ሳዴ እና የሂዝባላህ ገንዘብ አቅራቢ ኢብራሂም ጣህር እንዲሁም ሌሎች በጊኒ የሚንቀሳቀሱ ሊባኖሳዊ ነጋዴዎች በርካታ መጠን ያለው ገንዘብ በመያዝ በልዩ በረራ ከጊኒ ወደ ሊባኖስ በርረዋል፡፡ ቡድኑ ይህ ገንዘብ የሚውለው በሊባኖስ የኮቪድ-19 ሁኔታን ለማገዝ ብሏል፡፡ ቀደም ሲልም የኮቪድ-19 እርዳታ ለሂዝባላህ ከጊኒ ወደ ሊባኖስ ገንዘብ ለማስተላለፍ እንደ ሽፋን አገልግሏል፡፡

ሳዴ የአሳ ማጥመጃ ጀልባዎችን ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ናርኮቲክ ለማዘዋወር እንደሚጠቀም ይጠረጠራል፡፡

በየካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ሳዴ ለሂዝባላህ የማቴሪያል እገዛ፣ ስፖንሰር በማድረግ ወይም የቁሳቁስ ወይም የአገልግሎቶች ወይም ሌሎች ድጋፎችን ለሂዝባላህ ለማቅረብ የገንዘብ፣ የማቴሪያል ወይም የቴክኖሎጂ ድጋፍ በማድረግ ምክንያት ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሳዴ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሳዴ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

ምስሎች፡-

ፖስተሮች፡-

ተያያዥ ስፍራዎች፡-

Guinea

የልደት ቀን፡-

ግንቦት 10 ቀን 1934 ዓ.ም.

የልደት ቦታ፡-

ኮናክሬ፣ ጊኒ

ዜግነት፡-

ሊባኖስ

ብሔራዊ መታወቂያ ቁጥር/ሮች እና አገር፡-

RL0420013 (ሎባኖስ), አገልግሎቱ የሚያበቃበት ቀን፡- የካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም.፣ 14205180170519 (ጊኒ)፣ አገልግሎቱ የሚያበቃበት ቀን፡- ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም.፤ 18FV09784 (ፈረንሳይ)፣ አገልግሎቱ የሚያበቃበት ቀን፡-ጥር 29 ቀን 2021 ዓ.ም.

ጾታ፡-

ወንድ

ሌላ መጠሪያ ስም/አማራጭ የስም ፊደላት፡-

አሊ ሙሳ ሳዴ

SUBMIT A TIP

Do Your Part. Secure a Safer World.

There are many ways to submit information to Rewards for Justice.

You may choose from multiple platforms and contact us in numerous languages. To process your information efficiently, we ask you to state your information as succinctly as possible, provide your name, location, and preferred language, and upload all relevant files such as photographs, videos, and documents to support your information. An RFJ representative will soon contact you. Please be patient, as RFJ reads every tip we receive.

Please open your Line app to submit a tip. The number is +1 202 702 7843

Please open your Viber app to submit a tip. The number is +1 202 702 7843

Please visit our Tor-based tips-reporting channel at: he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion

መረጃ ይስጡ

የበኩልዎን ያድርጉ

መረጃ ለማቅረብ በርካታ መንገዶች አሉ፡፡

ከተለያዩ ፕላትፎርሞች ሊመርጡ እና በተለያዩ ቋንቋዎች ሊያገኙን ይችላሉ፡፡ የእርስዎን መረጃ በውጤታማነት ለማካሄድ እንዲችሉ፣ የሚሰጡትን መረጃ በተቻለ መጠን እጥር፣ ምጥን ባለ መልኩ እንዲያቀርቡ እንጠይቅዎታለን፤ እንዲሁም ስምዎን ፣ የሚገኙበትን ቦታ፣ የሚመርጡትን ቋንቋ እና እንደ ፎቶግራፍ፣ ቪድዮ እና ሰነዶች ያሉ የእርስዎን መረጃዎች የሚደግፉ ማስረጃዎች አፕሎድ እንዲያደርጉ ልንጠይቅዎ እንችላለን፡፡ የወሮታ ለፍትሕ ወኪልም በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገኝዎታል፤ እባክዎን በትዕግስት ይጠብቁን፤ ወሮታ ለፍተሕ እያንዳንዱን መረጃ ያነብባል፡፡

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን ሲግናል ማመልከቻዎን ይክፈቱለ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን Line ማመልከቻዎን ይክፈቱለ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን የቴሌግራም አፕሊኬሽንዎን ይክፈቱ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን የቫይበር አፕሊኬሽንዎን ይክፈቱ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

እባክዎን በቶር ላይ የተመሠረተ የመጃዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቻናላችንን በዚህ ያግኙ፡- he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion

Skip to content