ወሮታ ለፍትሕ ስለ ፋውድ ሙሀመድ ኻላፍ በሌላ ስሙ ፋዑድ ሾንጋሌ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ኻላፍ የአል-ሸባብ መሪ ሲሆን ለዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት (ኤፍቲኦ) ለተባለው የፋይናንስ ድጋፍ እንዲሰጥ አመቻችቷል፡፡
በሚያዝያ 2000 ዓ.ም. ኻላፍ እና በርካታ ሌሎች ግለሰቦች በኢትዮጵያ የጦር ሰፈሮች እና በሞቃዲሾ፣ ሶማሊያ በሚገኙ የሽግግር ፌዴራል መንግስት አካላት ላይ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ የተፈፀሙትን ጥቃቶች መርተዋል፡፡ በሜይ 2008 ኻላፍ እና የተዋጊዎች ቡድን በሞቃዲሾ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት በፈመፀም እና በመያዝ በበርካታ ወታደሮች ላይ የሞት እና የመቁሰል አደጋ አስከትለዋል፡፡ በዚያው ወር ኻላፍ በኪስማሃዮ፣ ሶማሊያ በሚገኙ መስጊዶች ሁለት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች አዘጋጅቷል፡፡
በሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ.ም. የዬኤስ የገንዘብ ሚኒስቴር ኻላፍ ልዩ ዜጋ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13536 መዝግቦታል፡፡ ለዚህም ምክንያት የሆነው በሶማሊያ ውስጥ ለተፈፀመ የሀይል ድርጊት እና የሰላም መናጋት አስተዋፅኦ በማድረጉ ነው፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የኻላፍ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከኻላፍ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አል-ሸባብ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡