ወሮታ ለፍትሕ ስለ ፋሩቅ አል-ሱሪ በሌላ ስሙ ሳሚር ሂጃዚ ወይም አቡ ሀማም አል-ሻሚ ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ሱሪ ሁራስ አል-ዲን (ኤችኤዲ) የተባለ የሽብር ድርጅት መሪ ሲሆን የአል-ቃዒዳ (ኤኪው) የረዥም ጊዜ አባል ነው፡፡
አል-ሱሪ ከአል-ቃዒዳ ከፍተኛ መሪ ሳዪፍ አል-አድል ጋር በመሆን በ1990ዎቹ በአፍጋኒስታን የፓራሚሊተሪ አሰልጣኝ ነበር፤ በተጨማሪም ከ1995-1997 ዓ.ም. በኢራቅ የአል-ቃዒዳ ተዋጊዎችን አሰልጥኗል፡፡ አል-ሱሪ ቀደም ሲል ከ2001-2005 ዓ.ም. በሊባኖስ ታስሮ ነበር፤ በኋላ የአል-ኑስራህ ግንባር (ኤኤንኤፍ) ወታደራዊ አዛዥ ሆነ፡፡ በ2008 ዓ.ም. ኤኤንኤፍን ለቆ ወጥቷል፡፡
በጳጉሜን 05 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ሱሪ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ሱሪ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ሱሪ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡