ጃማዓት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊም (ጄኤንአይኤም) ራሱን በማሊ የአል-ቃዒዳ ይፋዊ ቅርንጫፍ አድርጎ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ በ2009 ዓ.ም. በእሳላማዊ ማግሪብ የአል-ቃዒዳ የሰሃራ ቅርንጫፍ፣ አል-ሙራቢቶዉን፣ አንሳር አል-ዳይን እና ማሲና ነጻነት ግንባር በአንድነት ጃማዓት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊም (ጄኤንአይኤም)ን መሠረቱ፡፡ ይህ ድርጅት በማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ ለበርካታ ጥቃቶች እና ጠለፋዎች ኃላፊነት ይወስዳል፡፡ በሰኔ 2009 ዓ.ም.፣ ከባማኮ ወጣ ብሎ በምዕራባዊያን በሚዘወተር መዝናኛ ላይ ጥቃት ፈጸመ፤ እንዲሁም በየካቲት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. በኦዋጋዶዉጎዉ ላይ ለተፈጸመው የተቀናጀ ሰፊ ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል፡፡ በመስከረም ወር ጃማዓት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊም (ጄኤንአይኤም) በማዕከላዊ ማሊ በአውቶብስ ስር የተጠመደ ፈንጂ አፈንድቶ 14 ሲቪሊያኖች ሲገድል፣ 24 ደግሞ ቆስለዋል፡፡
በጳጉሜን 01 ቀን 2010 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጃማዓት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊም (ጄኤንአይኤም)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ቀደም ሲል በነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይሲስ-ኬን ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የጃማዓት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊም (ጄኤንአይኤም) ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከጃማዓት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊም (ጄኤንአይኤም) ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አጃማዓት ኑስራት አል-ኢስላም ዋል-ሙስሊም (ጄኤንአይኤም) ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡