ወሮታ ለፍትሕ የኢስላሚክ ኢስቴት በኢራቅ እና ሶሪያ (አይሲስ)ን የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎችን ለማቃወስ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አይሲስ እንቅስቃሴዎቹን ለማስቀጠል የፋይናንስ እና የማመቻቻ ኔትወርኮች ላይ የተመሠረተ ነው፤ ይህ ድርጅት በሶሪያ እና በዙሪያው ባለው ክልል ጥቃቶች ይፈጽማል፡፡
አይሲስ በኢንዶኔዢያ እና ቱርክ ገንዘብ በማሰባሰብ በሶሪያ ተፈናቃዮች ካምፖች የሚካሄዱ የአይሲስ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ ገንዘብ ያስተላልፋል፤ ከዚህ ገንዘብ መካከለ የተወሰነው ለአይሲስ የውጭ አገር ተዋጊዎችን ሆነው የሚያገለግሉ ልጆችን ከካምፖች በሕገወጥ መንገድ ለሚያስተላልፉ ክፍያ ለመፈጸም ጥቅም ላይ የውላል፡፡
ከ40 በላይ በሚሆኑ አገራት የሚገኙ የአይሲስ ደጋፊዎች አይሲስ ወደፊት ለሚያካሂዳቸው ወታደራዊ ጥቃቶች እንዲውል በዚህ ካምፕ ለሚገኙ ከአይሲስ ጋር ግንኙነት ላላቸው ሰዎች የገንዘብ ድጋፍ ልከዋል፡፡ አል-ሃውል የተባለው በሰሜን ምሥራቅ ሶሪያ ካሉ ካምፖች ትልቁ ካምፕ 70,000 የሚያህሉ ተፈናቃዮች የያዘ ሲሆን፣ በዚህ ካምፕ አይሲስ ደጋፊዎች በወር እስከ $20,000 በሃዋላ በኩል አግኝተዋል፡፡ ሃዋላ ኢመደበኛ የገንዘብ ማስተላለፊያ ዘዴ ነው፡፡ አብዛኞቹ እነዚህ የገንዘብ ማስተላለፍ ተግባራት ምንጫቸው ሶሪያ ወይም እንደ ቱርክ ባሉ ጎረቤት አገራት ያለፉ ናቸው፡፡
ከሶሪያ እና ኢራቅ የተዘረፉ የአርኪኦሎጂ ቁሳቁሶች ሕገወጥ ዝውውር አይሲስ የውጭ ምንዛሪ እንዲያገኝ እና ጭከና የተሞላባቸውን ታክቲኮቹን ለመፈጸም እና ንጹሃን ዜጎችን ለመጨቆን አስቻይ ከሆኑት ቁልፍ የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎቹ መካከል አንዱ ነው፡፡ አይሲስ በሶሪያ እና በኢራቅ ባሕላዊ እና ታሪካዊ ሳይቶች ላይ ያደረሰው ጉዳት እና ዘረፋ ሊተኩ የማይችሉ የጥንታዊ ሕይወት እና ኅብረተሰብ ማስረጃዎች እንዲጠፉ አድርጓል፡፡
ጥንታዊ እና ታሪካዊ ሳንቲሞች፣ ጌጣጌጦች፣ ቅርጽ የወጣላቸው ኖራ ድንጋዮች፣ ቅርጻ ቅርጾች፣ ጽሁፎች የተቀረጹባቸው ድንጋዮች፣ ጥንታዊያን ጽሑፎች አይሲስ ጥቃት ካደረባቸው ባሕላዊ ዕቃዎች መካከል ይካተታሉ፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተሰጠ ድጋፍ፣ ዓለም ዓቀፉ የሙዚየሞች ምክር ቤት ከሶሪያ እና ኢራቅ የተዘረፉ እና በሕገወጥ መንገድ የተላለፉ፣ ስጋት ላይ የሚገኙ ባሕላዊ ዕቃዎችን በተመለከተ ድንገተኛ ቀይ ዝርዝር አዘጋጅቷል፡፡