ወሮታ ለፍትሕ ስለ አይሲስ የእገታ ኔትወርክ ወይም ማኸር መህፉዝ፣ ሚካኤል ካያል፣ ግሪጎሪዮስ ኢብራሂም፣ ቦሎዉስ ያዚጊ እና ፓዎሎ ዳል’ኦግሊዮ እንዲገኙ፣ ያሉበት እንዲታወቅ ወይም እንዲመለሱ ለማድረግ የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
በየካቲት 02 ቀን 2005 ዓ.ም. የግሪክ ኦርቶዶክስ ቄስ ማኸር ማህፎውዝ እና አርመኒያዊው የካቶሊክ ቄስ ሚካኤል ካያል በካፍሩን፣ ሶሪያ ወደሚገኝ ገዳም በአውቶብስ እየተጓዙ ነበር፡፡ ከአሌፖ፣ ሶሮያ በግምት በ30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲደርሱ ተጠርጣሪ የአይሲስ አባላት ተሽከርካሪውን አስቁመው የተጓዦችን ሰነዶች ፈተሹ፤ በመቀጠል ማኸር ማህፎውዝ እና ሚካኤል ካያልን አስወረዷቸው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እነዚህን ሰዎች ያየ ወይም ስለእነርሱ የሰማ አልተገኘም፡፡
በሚያዝያ 14 ቀን 2005 ዓ.ም.፣ የሶሪያ ኦርቶዶክስ ሊቀጳጳስ ግሬጎሪየስ ኢብራሂም የግሪክ ኦርቶዶክስ ሊቀጳጳስ ቦሎዉስ ያዚጊን ለማምጣት ከአሌፖ ወደ ቱርክ ተጓዙ፡፡ በአል-ማንሶዉራ፣ ሶሪያ በሚገኝ የፍተሻ ጣቢያ ሲደርሱ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች አድፍጠው በመጠበቅ ይጓዙበት የነበረውን ተሽከርካሪ አስቆሙ፡፡ የኃይማኖት አባቶቹ ሾፈር በኋላ ሞቶ ተገኝቷል፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱ ከአል-ቃዒዳ ጋር ግንኙነት ባለው የአል-ኑስራ አባላት ታግተዋል ተብሎ ይታመናል፤ ነገር ግን በኋላ ሊቀጳጳሳቱ ለአይሲስ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡
በሐምሌ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. አይሲስ ጣሊያናዊውን የጁሪስት ቄስ ፓዎሎ ዳል’ኦግሊዮ በሶሪያ በሚገኘው ራቃህ በሚባል ስፍራ ጠልፎ ወሰደ፡፡ አባ ዳል’ኦግሊዮ፣ ማህፎዉዝ፣ ካያል፣ ኢብራሂም እና ያዚጊ እንዲለቀቁ ለመጠየቅ ከአይሲስ ጋር የመገናኘት ዕቅድ ነበራቸው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እርሳቸውን ያየ ወይም ስለ እርሳቸው የሰማ አልተገኘም፡፡