የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ይፋዊ ዌብሳይት

የአልሸባብ የፋይናንስ ኔትወርክ

አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ የሽብረተኛውን ድርጅት የአል-ሸባብን የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎች ለማሰናከል የሚያስቸል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ የአል-ሸባብ የፋይናንስ ኦፕሬሽን እና የማመቻቻ ኔትወርኮች የድርጅቱን ሥራዎች ለማስቀጠል እና የሽብር ጥቃቶቹን በገንዘብ ለማገዝ ያግዛሉ፤ ይህም ሁኔታ በሶማሊያ እና በጎረቤት አገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎችን እና የጸጥታ ኃይሎችን ለሞት ዳርጓል፡፡

አል-ሸባብ የተለመደውን ለሽብር የሚውል ገንዘብ ማግኛ ዘዴዎችን ለምሳሌ ግቦ መስጠት፣ ብዝበዛ፣ ሃዋላ የገንዘብ ማስተላለፍ፣ ገንዘብ ለማግኘት ማገት፣ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የግል አዘዋዋሪዎችን ይጠቀማል፡፡ ነገር ግን በሌላ በኩል የራሱን የገንዘብ ምንጮች ለማግኘት የቻለ ሲሆን፣ ከውጭ ከሚያገኛቸው የገንዘብ ምንጮች ራሱን ነጻ ለማድረግ ችሏል፡፡ ከአዲሶቹ የገንዘብ ምንጮቹም መካከል በእድሜ ከገፉ ሰዎች፣ ከነጋዴዎች እና ከገበሬዎች ገንዘብ መበዝበዝ፣ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ንግድ፣ በሞባይል ገንዘብ ማስተላለፍ እንዲሁም የአርብቶ አደሮችን ከብቶች መዝረፍ ይገኙባቸዋል፡፡ በግዛት ማስፋፋት አማካኝነትም አል-ሸባብ በሕገወጥ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ እንደ ከሰል ያሉ ማዕድናት እና ሄሮይን ሕገወጥ ንግድ ላይ ይሳተፋል (እነዚህንም ለወንጀለኛ ቡድኖች መልሶ ይሸጣል)፡፡ በተጨማሪም አል-ሸባብ በግለሰቦች፣ በባሕር ላይ ዘራፊዎች ወዘተ ላይ ግብር ይጥላል፤ በግብርና ምርቶች እና በመሬት ላይ ገንዘብ፣ ክፍያ እና ግብር ይሰበስባል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ የሚከለተውን ለማዛባት የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ ወሮታ ይከፍላል፡-

-ለአልሸባብ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ ምንጮች (ለምሳሌ ብዝበዛ እና ግብር፣ ኮንትሮባንድ በሕገወጥ መንገድ ማስገባት እና የጦር መሣሪያ እና የዕጽ ንግድ)

-በአልሸባብ የአገር ውስጥ የተፈጥሮ ኃብቶችን ማውጣት (ለምሳሌ የእነጨት ምርት፣ ማዕድን ማውጣ እና በሕገወጥ ማስገባት)

-በገንዘብ ረጂዎች እና በፋይናንስ አመቻቾች ለአልሸባብ የሚደረግ የፋይናንስ መዋጮዎች፤

-አልሸባብን በመወከል ገንዘብ ለማስተላለፍ አና ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቋማትን ተደራሽ ለማድረግ በፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ የገንዘብ ልውውጥ እና የገንዘብ አገልግሎት ሰጪዎችን መጠቀም፤

-በአልሸባብ ወይም በእርሱ የገንዘብ አቅራቢዎች ባለቤትነት ስር ያሉ የንግድ ድርጅቶች ወይም ኢንቬስትመንቶች፤

-ከአልሸባብ ጋር ትስስር ያላቸው፣ እርሱን በወመከል የፋይናንስ ልውውጦች የሚያካሄዱ ሽፋን ሰጪ ኩባንያዎችን እንቅስቃሴዎች (ለምሳሌ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ንግድ)፤

-የአልሸባብ አባላት እና ደጋፊዎቻቸው የሚሳተፉባቸው፣ ድርጅቱን በገንዘብ የሚጠቅሙ የወንጀል እንቅስቃሴዎች (ለምሳሌ ገንዘብ ለማስከፈል ሲባል የሚፈጸሙ እገታዎች እና የአርብቶ አደሮችን ክብቶች መዝረፍ)

-የአልሸባብ ሕገወጥ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎች (ለምሳሌ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር)፣ በአልሸባብ ለሽብርተኞቹ እና የእጅ አዙር ሚሊሻ እና አጋሮቹ የሚፈጸም ገንዘብ እና ዕቃዎች ማስተላለፍ፤

በመጋቢት 09 ቀን 2000 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አልሸባብን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ በኋላም በመጋቢት 10 ቀን 2000 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አልሸባብን ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአልሸባብ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአልሸባብ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም ለአልሸባብ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

ፖስተሮች፡-

ተያያዥ ስፍራዎች፡-

ሱማሊያ, ኬኒያ

SUBMIT A TIP

Do Your Part. Secure a Safer World.

There are many ways to submit information to Rewards for Justice.

You may choose from multiple platforms and contact us in numerous languages. To process your information efficiently, we ask you to state your information as succinctly as possible, provide your name, location, and preferred language, and upload all relevant files such as photographs, videos, and documents to support your information. An RFJ representative will soon contact you. Please be patient, as RFJ reads every tip we receive.

Please visit our Tor-based tips-reporting channel at: he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion

መረጃ ይስጡ

የበኩልዎን ያድርጉ

መረጃ ለማቅረብ በርካታ መንገዶች አሉ፡፡

ከተለያዩ ፕላትፎርሞች ሊመርጡ እና በተለያዩ ቋንቋዎች ሊያገኙን ይችላሉ፡፡ የእርስዎን መረጃ በውጤታማነት ለማካሄድ እንዲችሉ፣ የሚሰጡትን መረጃ በተቻለ መጠን እጥር፣ ምጥን ባለ መልኩ እንዲያቀርቡ እንጠይቅዎታለን፤ እንዲሁም ስምዎን ፣ የሚገኙበትን ቦታ፣ የሚመርጡትን ቋንቋ እና እንደ ፎቶግራፍ፣ ቪድዮ እና ሰነዶች ያሉ የእርስዎን መረጃዎች የሚደግፉ ማስረጃዎች አፕሎድ እንዲያደርጉ ልንጠይቅዎ እንችላለን፡፡ የወሮታ ለፍትሕ ወኪልም በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገኝዎታል፤ እባክዎን በትዕግስት ይጠብቁን፤ ወሮታ ለፍተሕ እያንዳንዱን መረጃ ያነብባል፡፡

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን ሲግናል ማመልከቻዎን ይክፈቱለ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን የቴሌግራም አፕሊኬሽንዎን ይክፈቱ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

እባክዎን በቶር ላይ የተመሠረተ የመጃዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቻናላችንን በዚህ ያግኙ፡- he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion

Skip to content