ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሮበርት ኤ. “ቦብ” ሌቪንሰን መገኛ፣ ማስመለስ እና መመለስ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $20 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ይህ ጡረታ የወጣ የኤፍቢአይ ስፔሻል ኤጀንት በየካቲት 30 ቀን 1999 ዓ.ም. በስራ ምክንያት ወደ ኪሽ ደሴት፣ ኢራን ከተጓዘ በኋላ ደብዛው ጠፍቷል፡፡ ሌቪንሰን በ1990 ከኤፍቢአይ በጡረታ የተገለለ ሲሆን በጠፋበት ጊዜ የግል መርማሪ በመሆን ይሰራ ነበር፡፡
በታኅሳስ 2013 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር በሌቪንሰን ጠለፋ ላይ ለነበራቸው ተሳትፎ በሁለት ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣኖች መሀመድ ባሲሪ እና አህመድ ኻዛይ ላይ ማዕቀብ ጥሏል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ አሁንም ሌሎች በዚህ ላይ ተሳትፎ ስለነበራቸው ሰዎች መረጃ ትፈልጋለች፡፡