ወሮታ ለፍትሕ ስለ ኸሊል አል-ራህማን ሃቃኒ፣ በሌላ ስሙ ኸሊል ሃቃኒ ወይም ኸሊል አህመድ ሃቃኒ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ኸሊል በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት (ኤፍቲኦ) ተብሎ የተመዘገበው ሃቃኒ ኔትወርክ (ኤችኪውኤን) ቁልፍ የአመራር አባል በመሆን አገልግሏል፡፡
ኸሊል ስለ ታሊባል በመሆን የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራዎች ይሰራል፤ እንዲሁም በአፍጋኒስታን ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የታሊባን አባላት ድጋፍ ይሰጣል፡፡ በ2002 ዓ.ም. መግቢያ፣ በአፍጋኒስታን፣ ሎጋር ክፍለ አገር ለሚገኙ የታሊባን ህዋሳት የገንዘብ ድጋፍ ሰጥቷል፡፡ በ2001 ዓ.ም. ደግሞ በታሊባን እና በኤችኪውኤን ለተያዙ ሰዎች እስር በኃላፊነት ከሚጠየቁ በርካታ ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ኸሊል በጠቅላላው የሃቃኒ ኔትወርክ መሪ እና የታሊባን ምክትል መሪ ከሆነው ከወንድሙ ወይም እህቱ ልጅ ሲራጁዲን ሃቃኒ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ለታሊባን ኦፕሬሽኖች አካሂዷል፡፡ በ1994 ዓ.ም. በፓክቲያ ክፍለ አገር፣ አፍጋኒስታን አል-ቃዒዳ አባላትን ለማጠናከር ተዋጊዎችን አሰማርቷል፡፡
በየካቲት 02 ቀን 2003 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኸሊል ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የኸሊል ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከኸሊል ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው የሃቃኒ ኔትወርክ (ኤችኪውኤን) ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡