ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ኢብራሒም ጣህር በጊኒ የሚገኝ የሂዝባላህ ገንዘብ አቅራቢ ነው፡፡ ጣህር በጊኒ ከሂዝባላህ ዋና ዋና ገንዘብ አቅራቢዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ከሂዝባላህ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሰዎችን በርካታ ሰዎች እንደሚጠቀም ይታመናል፡፡
ጣህር እና አንድ ተባባሪው ከንግድ ተቋሞቻቸው መካከል በአንዱ የተሰበሰበ የአሜሪካ ዶላር ወደ ኮናክሬ አየር ማረፊያ ልኮ፣ ለጊኒ ለጉምሩክ ኃላፊዎች መደለያ ገንዘብ በማቅረብ የያዙት የውጭ ምንዛሪ በሻንጣ ውስጥ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡ ጣህር ወደ ጊኒ እና ከጊኒ ውጪ በሚጓዝበት ወቅት በኮት ዲቯር የሊባኖስ የክብር ምክር ቤት አባልነቱን ተጠቅሟል፡፡
በቅርቡ በ2012 ዓ.ም. ሳዴ እና የሂዝባላህ ገንዘብ አቅራቢ ኢብራሂም ጣህር እንዲሁም ሌሎች በጊኒ የሚንቀሳቀሱ ሊባኖሳዊ ነጋዴዎች በርካታ መጠን ያለው ገንዘብ በመያዝ በልዩ በረራ ከጊኒ ወደ ሊባኖስ በርረዋል፡፡ ቡድኑ ይህ ገንዘብ የሚውለው በሊባኖስ የኮቪድ-19 ሁኔታን ለማገዝ በማለት ፍተሻን ለማለፍ ችሏል፡፡ ቀደም ሲልም የኮቪድ-19 እርዳታ ለሂዝባላህ ከጊኒ ወደ ሊባኖስ ገንዘብ ለማስተላለፍ እንደ ሽፋን አገልግሏል፡፡
በየካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ጣህር ለሂዝባላህ የማቴሪያል እገዛ፣ ስፖንሰር በማድረግ ወይም የቁሳቁስ ወይም የአገልግሎቶች ወይም ሌሎች ድጋፎችን ለሂዝባላህ ለማቅረብ የገንዘብ፣ የማቴሪያል ወይም የቴክኖሎጂ ድጋፍ በማድረግ ምክንያት ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የጣህር ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከጣህር ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡