ወሮታ ለፍትሕ በ2010 ዓ.ም. በቶንጎ ቶንጎ ኒጀር ጥቃት ለይ ተሳትፎ ስለነበረው ስለ ኢብራሂም ኦዉስማን፣ በሌላ ስሙ ዳንዶዉ ቼፎዉ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ወሮታ ይከፍላል፡፡ ኢብራሂም ኦዉስማን የአይሲስ-ግሬተር ሳሃራ (አይሲስ-ጂኤስ) አዛዥ ነው፡፡
በመስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በቶንጎ ቶንጎ መንደር አቅራቢያ፣ ኒጀር፣ ከአይሲስ ግሬተር ሰሃራ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ለናይጄሪያ የጸጥታ ኃይል ሽብርን ስለመዋጋት ሥልጠና፣ ምክር እና እገዛ በመስጠት ላይ በነበረ የዩናይትድ ስቴትስ ስፔሻል ፎርስ ላይ ጥቃት ፈጽሟል፡፡ በዚህም ጥቃት ምክንያት አራት አሜሪካዊያን እና አራት ናይጄሪያዊያን ወታደሮች ሞተዋል፡፡ በዚህ ጥቃት ሁለት ተጨማሪ አሜሪካዊያን እና ስምንት ናይጄሪያዊያን ቆስለዋል፡፡ በጥር 04 ቀን 2010 ዓ.ም. የአይሲስ- ጂኤስ መሪ አድናን አቡ ዋሊድ አል-ሳህራዊ ለዚህ ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል፡፡