ወሮታ ለፍትሕ ስለ ኢብራሂም ሳሊህ መሐመድ አል-ያቁብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ናስር የሳውዲ ሂዝባላህ ሽብርተኛ ድርጅት አባል ነው ተብሎ የሚነገርለት ሲሆን፣ በ1988 በሳውዲ አረቢያ፣ በዳህራን አካባቢ በሚገኙ ኮባር መንትያ ህንፃዎች ላይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ላይ ለነበረው ሚና ይፈለጋል፡፡
በሰኔ 18 ቀን 1988 ዓ.ም. የሳውዲ ሂዝባላህ አባላት በኮባር መንትያ ህንፃዎች (በዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ አባላት በመኖሪያነት ጥቅም ላይ የሚውል) የተሽከርካሪ ማቆሚያ በፕላስቲክ የተሰሩ ፈንጂዎች የያዘ ቦቴ ተሽከርካሪ ላይ የቦምብ ፍንዳታ ፈጽመዋል፡፡ በዚህ ፍንዳታ ምክንያት በአካባቢው የሚገኘውን ህንፃ አውድሞ 19 የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች እና አንድ የሳውዲ ዜጋ ሲሞቱ፣ የተለያዩ ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች ላይ መቁሰል አስከትሏል፡፡
በሰኔ 14 ቀን 1993 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ግራንድ ጁሪ አልናስር እና 13 ሌሎች ከጥቃቱ ጋር የተያያዙ ግለሰቦች እንዲከሰሱ ወስኗል፡፡
በጥቅምት 2 ቀን 1994 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አልናስር አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአልናስር ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአልማግሪቢ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡