የእስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራተዊት (አይአርጂሲ) የኢራን ይፋዊ የጦር ሠራዊት አካል ሲሆን፣ ኢራን ሽብርተኝነትን የመንግሥቷ የአሰራር አካል አድረጋ በመጠቀሙ ረገድ ባላት ሚና ላይ ማዕከላዊ ሚና ይጫወታል፡፡ በተጨማሪም አይአርጂሲ በዓለም ዙሪያ ሽብርተኝነትን ያቅዳል፣ ያደረጋጃል እንዲሁም ይፈጽማል፡፡ በተጨማሪም አይአርጂሲ በዓለም ዙሪያ ሌሎች የሽብር ቡድኖችን ፈጥሯል፣ ደግፏል እንዲሁም መርቷል፡፡ አይአርጂሲ አሜሪካን እና የአሜሪካን ተቋማት፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች የሞቱባቸውን በርካታ ጥቃቶች ፈጽሟል፡፡ አይአርጂሲ በ1971 ዓ.ም. ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የኢራንን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መፈጸም ረገድ ከፍተኛ ሚና ነበረው፡፡ ይህ ቡድን በአሁኑ ጊዜ በኢራን ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ የተቆጣጣሪነት ሚና አለው፤ እንዲሁም በኢራን የአገር ውስጥ ፖሊሲዎች ውስጥ ተጽዕኖ ያስከትላል፡፡
በሚያዝያ 07 ቀን 2011 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የእስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራተዊት (አይአርጂሲ)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ በኋላም በጥቅምት 21 ቀን 1994 ዓ.ም. ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይአርጂሲ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአይአርጂሲ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአይአርጂሲ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አይአርጂሲ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡