የኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት -ቆድስ ኃይል (አይአርጂሲ-ኪውኤፍ) የአይአርጂሲ አካል ሲሆን፣ ኢራን በውጭ አገራት የሚገኙ የሽብር ቡድኖችን የምታጎለብትበት እና የምትደግፍበት ዋነኛ ዘዴ ነው፡፡ ኢራን የኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት -ቆድስ ኃይልን በመጠቀም የውጭ ፖሊሲ ግቦቿን ለመተግበር፣ ለስለላ ሥራዎች ሽፋን ለመስጠት እና በመካከለኛው ምሥራቅ አለመረጋጋት እንዲሰፍን ትሰራበታለች፡፡ በ2003 ዓ.ም. የኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት -ቆድስ ኃይል በዋሽንግተን ዲ.ሲ የሳውዲን አምባሳደር ለመግደል አሴረ፡፡ በ2004 ዓ.ም. የኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት -ቆድስ ኃይል አባላት ጥቃቶችን ለመፈጸም በማሴር ሲንቀሳቀሱ በቱርክ እና ኬኒያ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ በጥር 2010 ዓ.ም. ጀርመን የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም ሲያሴሩ የነበሩ 10 የኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት -ቆድስ ኃይል አባላትን በቁጥጥር ስር አውላለች፡፡
በሚያዝያ 07 ቀን 2011 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአይአርጂሲ-ቆድስ ኃይልን ጨምሮ የእስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራተዊት (አይአርጂሲ)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ በኋላም በጥቅምት 21 ቀን 1994 ዓ.ም. ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይአርጂሲን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአይአርጂሲ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአይአርጂሲ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አይአርጂሲ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡