ወሮታ ለፍትሕ ኢሳ ጂማራዉ በ2010 ዓ.ም. በቶንጎ ቶነጎ፣ ኒጀር ጥቃት ላይ ለነበረው ተሳትፎ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ኢሳ ጂማራዉ የአይሲስ-ግሬተር ሰሃራ (አይሲስ-ጂኤስ) አባል ሲሆን፣ ተጠሪነቱ ለአይሲስ አዛዦች ኦዉስማን ኢሊአሶዉ ጂቦ፣ በሌላ ስሙ ፔቲት ቻፖሪ እና ኢሳ ባሬ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡
በመስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በቶንጎ ቶንጎ መንደር አቅራቢያ፣ ኒጀር፣ ከአይሲስ ግሬተር ሰሃራ ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች ለናይጄሪያ የጸጥታ ኃይል ሽብርን ስለመዋጋት ሥልጠና፣ ምክር እና እገዛ በመስጠት ላይ በነበረ የዩናይትድ ስቴትስ ስፔሻል ፎርስ ላይ ጥቃት ፈጽሟል፡፡ በዚህም ጥቃት ምክንያት አራት አሜሪካዊያን እና አራት ናይጄሪያዊያን ወታደሮች ሞተዋል፡፡ በዚህ ጥቃት ሁለት ተጨማሪ አሜሪካዊያን እና ስምንት ናይጄሪያዊያን ቆስለዋል፡፡ በጥር 04 ቀን 2010 ዓ.ም. የአይሲስ- ጂኤስ መሪ አድናን አቡ ዋሊድ አል-ሳህራዊ ለዚህ ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል፡፡