አይሲስ ኢን ዘ ግሬተር ሰሃራ (አይሲስ-ጂኤስ) የተመሠረተው ከአል-ቃዒዳ ተገንጥሎ የወጣው አል-ሙራቢቶዉን ከተገነጣጠለ በኋላ ነበር፤ ይህ ቡድን ለአይሲስ ያለውን ታማኝነት አረጋግጧል፡፡ በዋናነት በማሊ የሚገኘው እና በማሊ እና ኒጀር ድንበር ላይ የሚንቀሳቀሰው ይህ ቡድን በቡርኪናፋሶም በንቃት ይንቀሳቀሳል፡፡ አይሲስ-ጂኤስ ለበርካታ ጥቃቶች ኃላፊነት ወስዷል፤ ከእነርሱም መካከል በመስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በቶንጎ ጎንጎ፣ ኒጀር በዩናይትድ ስቴትስ እና ናጄሪያ ፓትሮል ላይ በፈጸመው ጥቃት አራት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች እና አራት የናይጄሪያ ወታደሮች ሞተዋል፡፡ በኅዳር 2011 ዓ.ም. አይሲስ-ጂኤስ ለ54 ወታደሮች ሞት ምክንያት የሆነውን ጥቃት በማሊ ሠራተዊት ላይ ጥቃት ፈጽሟል፡፡
በግንቦት 15 ቀን 2010 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይሲስ-ጂኤስን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ቀደም ብሎም በጥቅምት 21 ቀን 1994 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይሲስ-ጂኤስ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአይሲስ-ጂኤስ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአይሲስ-ጂኤስ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አይሲስ-ጂኤስ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡