ወሮታ ለፍትሕ ስለ አዚዝ ሀቃኒ በሌላ ስሙ አብዱል አዚዝ ሀቃኒ ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አዚዝ የሀቃኒ ኔትዎርክ (ኤችኪውኤም) ቁልፍ መሪ ነው፤ ይህ ኔትዎርክ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት (ኤፍቲኦ) ተብሎ ተመዝግቧል፣ ይህ ግለሰብ የሲራጁን ሀቃኒ (የኤችኪውኤን መሪ እና የታሊባን ምክትል መሪ) ወንድም ነው (ሀይፐርሊንክ)፡፡
አዚዝ በአፍጋን መንግስት ኢላማዎች ላይ በፈንጂዎች አማካይነት ጥቃት በማቀድ እና በመፈፀም ውስጥ ተሳትፎ አድርጓል፤ ወንድሙ ባሩዲን ሀቃኒ ከሞተ በኋላ ለሁሉም ዋና ዋና በኤችኪውኤን ለተፈፀሙ ጥቃቶች ሀላፊነት ወስዷል፡፡ አዚዝ በአፍጋን እና በአፍጋኒስታን- ፓኪስታን ድንበር ባሉ ጥምር ሀይሎች ላይ ለሚፈፀሙ ጥቃቶች የኦፕሬሽን እና የእዝ ውሳኔዎች ሀላፊነት ወስዷል፡፡ ለዚህም ሌላ በካቡል በመላው አፍጋኒስታን ለተካሄዱ ከፍተኛ ትኩረትን የሳቡ ጥቃቶች ዋነናው የኤችኪውኤን አገናኝ በመሆን አገልግሏል፡፡
በነሐሴ 19 ቀን 2007 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዚዝ ሀቃኒ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአዚዝ ሀቃኒ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአዚዝ ሀቃኒ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ኤችኪውኤን ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡