ወሮታ ለፍትሕ ስለ አብዲቃድር መሀመድ አብዲቃድር፣ በሌላ ስሙ ኢክሪማ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $3 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አብዲቃድር የአል-ሸብዓብ ከፍተኛ መሪ ሲሆን የኦፕሬሽን እና ሎጅስቲክስ ሀላፊ በመሆን አገልግሏል፡፡ አብዲቃድር ለአል-ሸብዓብ የቀድሞ ጥቃት እቅድ የማውጣቱን ተግባር መርቷል፣ የኬንያን ወጣቶች ለአል-ሸባብ በመመልመል ሂደት የአስተባባሪነት ሚና ተጫውቷል፣ በሶማሊያ የአል-ሸባብን የኬንያን ተዋጊዎች አዟል፡፡
በሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አብዲቃድር ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአብዲቃድር ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአብዲቃድር ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አል-ሸባብ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡