ወሮታ ለፍትሕ ስለ አብዱል ዋሊ በሌላ ስሙ ኦማር ኻሊድ ቆራሲኒ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $3 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ዋሊ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ከተሰየው የተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን (ቲቲፒ) ጋር ግንኙነት ያለው ወታደራዊ ክንፍ የሆነው ጃማት ኡል-አህራር (ጄዩኤ) መሪ ነው፡፡ በዋሊ አማር ስር ጄዩኤ በፑንጃብ ክፍለ ሀገር፣ ፓኪስታን በከፍተኛ ንቃት ከሚንቀሳቀሱት የቲቲፒ ኔትዎርኮች መካከል አንዱ ነው፤ ይህም በመላ ፓኪስታን ውስጥ ለተፈፀሙ በርካታ ጥቃቶች ሃላፊነት ይወስዳል፡፡
ዋሊ በአሁኑ ጊዜ በአፍጋኒስታን ናንጋርሀር እና ኩናር ክፍለ ሀገሮች በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ይባላል፡፡ ዋሊ በፓኪስታን በሚገኘው መሀመድ ኤጀንሲ ውስጥ ተወለደ፡፡ ከዚህ ቀደም በጋዜጠኝነት ሲሰራ የነበረ ሲሆን በበርካታ የካራቺ፣ ፓኪስታን መድረሳዎች ተምሯል፡፡