ወሮታ ለፍትሕ ስለ አብደልበሲጥ አልሀጅ አልሀሰን ሀጅ ሀማድ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አብደልበሲጥ በታኅሳስ 22 ቀን 2000 ዓ.ም. በካርቱም የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤድ) ሰራተኞች በነበሩት ጆን ግራንድቪል እና አብደልራህማን አባስ ራሃማ ግድያ ላይ ከተሳተፉት ታጣቂዎች መካከል አንዱ በሚል ይፈለጋል፡፡
የሱዳን ፍርድ ቤት በ2009 በእነዚህ የግድያ ወንጀሎች ላይ በመሳተፉ ምክንያት ወንጀለኛ ነው በማለት የሞት ቅጣት ወስኖበታል፡፡ ሆኖም ግን አብደልበሲጥ በሰኔ 03 ቀን 2002 ዓ.ም. የተወሰነበት ቅጣት ከመፈፀሙ በፊት ከእስር ቤት አምልጧል፡፡ አሁንም አልተያዘም፤ በሱማሊያ ይገኛል ተብሎ ይታመናል፡፡
በታኅሳስ 30 ቀን 2005 ዓ.ም.. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አብዱልበሲጥ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአብዱልበሲጥ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአልማግሪቢ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡