ወሮታ ለፍትሕ ስለ አቡ ኡባይዳህ ዩሱፍ፣ አል-አናቢ በሌላ ስሙ አቡ ኦቤይዳ ዩሱፍ አል-አናቢ እና ያዚድ ሙባረክ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $7 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-አናቢ የአል-ቃዒዳ የኢዝላሚክ ማግሪብ (ኤኬውአይኤም) የሽብር ድርጅት መሪ ነው፡፡ ኤኪውአይኤም አል-አናቢ የቡድኑ አዲሱ መሪ መሆኑን በኅዳር 2013 ዓ.ም. አሳወቀ፡፡ አል-አናቢ ስለ ኤኪውአይኤም በመሆን የአል-ቃዒዳ (ኤኪው) መሪ ለሆነው አይመን አል-ዛባሂሪ ታማኝ መሆኑን ገልፅዋል፡፡ በመሆኑም በአል-ቃዒዳ አለም አቀፍ እንቅስቃሴ አመራር ውስጥ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አል-አናቢ የአልጄሪያ ዜግነት ያለው ሲሆን ከዚህ ቀደም የኤኪአይኤም ከፍተኛ ምክር ቤት መሪ እና በኤኪውአይኤም ሹራ ምክር ቤት ያገለግል ነበር፡፡ አል አናቢ ከዚህ ቀደም የኤኪውአይኤም የሚዲያ ሀላፊ ነበር፡፡
በጳጉሜን 04 ቀን 2007 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-አናቢን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-አናቢ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአልአናቢ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በተጨማሪም፣ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ የሽብር ድርጅት ተብሎ ለተሰየመው ለኤኪውአይኤም ሆነ ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ ወይም ለማቅረብ መሞከር ወይም መመሳጠር የወንጀል ድርጊት ነው፡፡ አል-አናቢ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ቁጥር 1267/ዩኤንኤስሲአር1267/ በየካቲት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. በማዕቀብ ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፤ ስለሆነም የዚህ ግለሰብ ንብረቶች በአለም አቀፍ ደረጃ የታገዱ ሲሆን፣ የጉዞ እቀባ እና የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ተጥሎበታል፡፡