ወሮታ ለፍትሕ ስለ አቡ አብድ አል-ካሪመረ አል-ማስሪ በሌላ ስሙ ካሪም ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ማስሪ የአል-ቃዒዳ (ኤኪው) የረዥም ጊዜ አባል ሲሆን፣ ከአል-ቃዒዳ ጋር ትብብር ያለው የጅሀድ ቡድን ሁራስ አል-ዲን (ኤችኤዲ) ከፍተኛ መሪ ነው፡፡ በ2010 ዓ.ም. አል-ማስሪ የቡድኑ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው የሹራ ምክር ቤት አባል ነበር፤ ኤችኤዲ ተገንጥሎ የወጣበት አል-ቃዒዳ ጋር ግንኙነት ያለው አልቃፊ ቡድን ሀያት ታህሪን አል-ሻም እና በኤችኤዲ መካከል በሸምጋይነት መካከል አገልግሏል፡፡