ወሮታ ለፍትሕ፣ የአቡ አሊ አል-ቱኒዚን ማንነት ለመለየት ወይም አድራሻውን ለማግኘት የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ቱኒዚ በዩናይትድ ስቴትስ እና በውጭ አገር በሚገኙት ጥቅሞቹ ላይ ስጋት መደቀኑን የቀጠለው በኢስላሚክ ኢስቴት በኢራቅ እና አሽ-ሻም (አይሲስ) ቁልፍ መሪ ነው፡፡
አቡ አሊ አል-ቱኒዚ በኢራቅ የአይሲስ ማምረቻ መሪ ነው፡፡ ለአይሲስ አባላት ሥልጠና የሰጠ ሲሆን፣ ከሰጣቸው ስልጠናዎችም መካከል የፈንጂዎች፣ ራስን በራስ የማጥፋት ተግባር ለመፈጸም ስለሚያገለግሉ ነገሮች እና ስለድብቅ ፈንጂዎች አስራር ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ አል-ቱኒዚ ስለ ጦር መሣሪያዎች ማጎልበት እና ስለኬሚካል መሣሪያዎች አመራረት ከፍተኛ ደረጃ ያለው ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
አቡ አሊ በቀኝ እጁ እጁ እና በቀኝ ዓይኑ ላይ ጉዳቶች አሉበት፡፡
በታኅሳስ 08 ቀን 1997 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይሲስን (ቀደም ሲል ኤኪውአይ ተብሎ የሚታወቅ) በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡