አቡ ኒዳል ድርጅት (ኤኤንኦ) የተመሠረተው ከፍልስጤም ሊብሬሽን ፍሮንት ተገንጥሎ በ1966 ዓ.ም. ነበር፡፡ ኤኤንኦ እስራኤል መጥፋት አለባት የሚል እምነት ነበረው፤ የመካከለኛውን ምሥራቅ የሰላም ሂደት ከመስመሩ ማስወጣት ከአላማዎቹ መካከል ነበር፡፡ ይህ ቡድን ለበርካታ የሽብር ጥቃቶች ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን፣ ከእነርሱም መካከል የቲደብልዩኤ በረራ 840 የቦንብ ጥቃት እና የፓን አም በረራ 73 ጠለፋ ይገኙባቸዋል፡፡
በመስከረም 28 ቀን 1990 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤኤንኦን በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በማለት በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት ሰይሞታል፡፡ በግንቦት 24 ቀን 2009 ዓ.ም. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኤኤንኦን የሽብርተኝነት አሰያየም ሰርዟል፡፡