ወሮታ ለፍትሕ ስለ አቡ ሁዜይፋ በሌላ ስሙ ሂጎ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ይህ ግለሰብ በቶንጎ ቶንጎ፣ ኒጀር ውስጥ በ2009 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት ተሳትፎ ነበረው፡፡ አቡ ሁዜይፋ የአይሲስ –ታላቁ ሳሃራ (አይሲስ-ጂኤስ) አዛዥ ነው፡፡
በመስከረም 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ቶንጎ ቶንጎ በተባለው የኒጀር መንደር አካባቢ ከአይሲስ –ግሬተር ሰሃራ (አይሲስ-ጂኤስ) ጋር ግንኙነት የነበራቸው ታጣቂዎች ሽብርተኝነትን በመዋጋት ላይ ለነበሩ የናይጄሪያ ሀይሎች ስልጠና፣ ምክር እና እገዛ ለመስጠት ተመድቦ በነበረው የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ሀይል ላይ የደፈጣ ጥቃት ፈፅሟል፡፡ በዚህ ጥቃት ምክንያት አራት የዩናይትድ ስቴትስ እና አራት የናይጄሪያ ወታደሮች ሞተዋል፡፡ በዚህ ጥቃት ሁለት ተጨማሪ አሜሪካውያን እና ስምንት ናይጄሪያውን ቆስለዋል፡፡ በጥር 04 ቀን 2010 ዓ.ም. የአይሲስ-ጂኤስ መሪ አድናን አቡ ዋሊድ አል-ሳህራዊ ለጥቃቱ ሀላፊነት ወስዷል፡፡