አል-ሸባብ ከአል-ቃዒዳ (ኤኪው) ጋር ተባባሪ ድርጅት ሲሆን፣ እንደ አል-ቃዒዳ በአረብ ባሕረሰላጤ እና አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ ያሉትን ጨምሮ ኬሎች ከአል-ቃዒዳ ተባባሪ ድርጅቶች ጋር ትስስር አለው፡፡ አል-ሸባብ በ1998 ዓ.ም. ሁለተኛ አጋማሽ የደቡብ ሶማሊያ ክፍሎችን በቁጥጥሩ ስር አውሎ ነበር፡፡ ከ1998 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ አልሸባብ እና ተባባሪ ሚሊሻዎች የደፈጣ ውጊያ እና ሌሎች የሽብርተኞች ታክቲኮች በመጠቀም በሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ላይ ኃይል መጠቀም ጀመረ፡፡
አልሸባብ በሶማሊያ፣ ኬኒያ፣ ኡጋንዳ እና ጅቡቲ ጥቃቶች ፈጽሟል፡፡ አል-ሸባብ በካምፓላ በሐምሌ 04 ቀን 2002 ዓ.ም. ለተፈጸሙት የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡ በዓለም ዋንጫ ጊዜ የተፈጸመው ይህ ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋን ጨምሮ 76 ሰዎችን ገድሏል፡፡ በመስከረም 2006 ዓ.ም. አል-ሸባብ በናይሮቢ በሚገኘው ዌስትጌት ሞል ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽሟል፡፡ ይህ ለበርካታ ቀናት የቆየው እገታ ቢያንስ የ65 ሲቪል ዜጎችን፣ የስድስት ወታደሮች እና ፖሊሶች ሕይወት ሲቀጥፍ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩት ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ በሚያዝያ 2007 ዓ.ም. አል-ሸባብ አነስተኛ የጦር መሣሪያዎች በመጠቀም እና ቦምቦች በመጠቀም በኬኒያ ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ላይ ጥቃት የፈጸመ ሲሆን፣ ይህ ጥቃት የ148 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል፡፡
ሚኒስቴር አል-ሸባብን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ በኋላም በመጋቢት 10 ቀን 2000 ዓ.ም. ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ሸባብን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ሸባብ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ሸባብ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አል-ሸባብ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡