ወሮታ ለፍትሕ የሂዝባላህ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አሊ ዩሰፍ ቻራራ በሌላ ስሙ አሊ ዩሰፍ ሻራራ እና “አሊ ዩሱፍ ሻራራ” ቁልፍ የሂዝባላህ ገንዘብ አቅራቢ እና በሊባኖስ የሚገኘው ስፔክትረም ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሆልዲንግ ኤስ.ኤ.ኤል ተብሎ የሚታወቀው፣ በዩናይትድ ስቴትስ የየገንዘብ ሚኒስቴር ማዕቀብ የተጣለበት የቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያ ሊቀመንበር ዋና ስራ አስኪያጅ ነው፡፡ ቻራራ ለዚህ ሽብረተኛ ቡድን የፋይናንስ ድጋፍ በሚያደርጉ የንግድ ፕሮጀክቶች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርግ ከሂዝባላህ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አግኝቷል፡፡
በተጨማሪም ቻራራ ስለ ሂዝባላህ የንግድ ኢንቨስትመንቶች ያመቻቻል፣ ቻራራ በኢራቅ በሚገኙ የንግድ እንቅስቃሴዎች ይሳተፋል፡፡ በተጨማሪም ቻራራ በምዕራብ አፍሪካ ሰፋፊ የቴሌኮሙኒኬሽን የንግድ ጥቅሞች አሉት፡፡
በታኅሳስ 28 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የየገንዘብ ሚኒስቴር ቻራራ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአቻራራ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከቻራራ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡