ወሮታ ለፍትሕ የሂዝባላህ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አሊ ቃሲር በኢራን የሂዝባላህ ወኪል እና የኢራን ኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ኮር – ቆድስ ፎርስ (አይአርጂሲ-ኪውኤፍ) እና ሂዝባላህ የፋይናንስ እና የንግድ እንቅስቃሴዎች ቁልፍ አመቻች ነው፡፡ እንዲሁም የሂዝባላህ ሀላፊ የሆነው ሙሀመድ ቃሲር የወንድም/የእህት ልጅ ሲሆን፣ በአይአርጂሲ-ኪውኤፍ እና በሂዝባላህ መካከል የፋይናንስ እንቅስቃሴዎችን ለማመቻቸት በቅርበት ይሰራል፡፡
አል-ቃሲር ታላቂ ግሩፕ በመባል የሚታወቀውን ከሂዝባላህ ጋር ተያያዠ የሆነ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነው፡፡ ይህ ኩባንያ ለአይአርጂሲ-ኪውኤፍ የሚደረጉ የነዳጅ ጭነቶችን በፋይናንስ ይደግፋል፡፡ ከአል-ቃሲር ሀላፊነቶች መካከል የእቃዎች የሽያጭ ዋጋ ላይ ድርድር ማድረግ እና ከጭነት መርከብ ጋር ተያያዥ የሆኑ ክፍያዎችን መፈፀም ይገኙበታል፡፡ አል-ቃሲር የሽያጭ ዋጋዎች ድርድር ላይ በበላይነት መርቷል፤ ለአይአርጂሲ-ኪውኤፍ ጥቅም ሲባል በአድሪያን ዳሪያ 1 ለተደረጉ የኢራን የነዳጅ ጭነቶች ወጪ ሸፍኗል፣ አመቻችቷል፣አሊ ቃሲር በሊባኖስ የሚገኝ ሆኮል ኤስ.ኤ.ኤልን የውጭ አገር ኩባንያ በመወክለ የኢራንን ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ለሶሪያ በማቅረብ ጉዳይ ላይ ድርድሮች ያካሂዳል፡፡ በተጨማሪም አሊ -ቃሲር ታላቂ ግሩፕን በመጠቀም የ10 ሚሊዮኖች ዶላር ዋጋ ያለው ብረት ሽያጭን አመቻችቷል፡፡
በነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አሊቃሲር ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአሊቃሲር ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአሊቃሲር ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ሂዝባላህ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡