ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሀላም አህመድ አል-ታማሚ በሌላ ስሟ “ኻልቲ” እና “ኻላቲ” ተብላ ስለምትታወቅ ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፤ ይህች ግለሰብ በ1985 በመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ድርድርን በመቃወም በ1993 በፈፀመችው የሀይል ድርጊት ምክንያት የቀረበው ወሮታ አካል ነው (ሀይፐርሊንክ)፡፡
በነሐሴ 03 ቀን 1993 ዓ.ም. አል-ታሚሚ አንድ ቦምብ እና የሀማስ አጥፍቶ ጠፊ ብዙ ህዝብ ወደተሰበሰበበት ስባሮ ፒዜሪያ አጓጓዘች፤ ይህ አጥፍቶ ጠፊ ፈንጂዎቹን አፈነዳ፡፡ ይህ ፍንዳታ ሰባት ህፃናትን አካትቶ 15 ሰዎችን ገድሏል፡፡ ጁዲት ሻና ግሪንባዉም የተባለች የ31 አመት እድሜ ያላት መምህርት እና የአስራ አምስት አመት እድሜ የነበራት ማርቻ ቻና ሮት የተባሉ አሜሪካውያን ከተገደሉት መካከል ነበሩ፡፡ ከ120 በላይ የሆኑት ደግሞ አራት አሜሪካውያንን ጨምሮ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ሀማስ በዚህ የቦንብ ፍንዳታ ሀላፊነቱን ወስዷል፡፡
አል-ታሚሚ ቀደም ሲል የቴሌቭዥን ጋዜጠኛ የነበረች ተማሪ ስትሆን፣ የሀማስ ወታደራዊ ክንፍ ኢዘዲን አል-ቃሲም ብርጌድስን በመወከል ጥቃቶች ለመፈፀም ቃል ከገባች በኋላ ቦምብ አፈንጂውን ይዛ ሄዳለች፤ይህም በኤፍቢአይ በሚገኘው መረጃዎች መሰረት ነው፡፡ አል-ታሚሚ እንዲሁም በስባሮ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አቅዳ መርታለች፤ ይህንን ቦታ የመረጠችበት ምክንያት በርካታ ሰዎችን የሚያስተናግድ ሬስቶራትን ስለሆነ ነው፡፡ ጥርጣሬን ለመቀነስ ቦምብ አፈንጂውን እንደ እስራኤላዊ እንዲለብስ አድርጋ ቦምቡን ራሷ አጓጉዛለች፡፡ ይህ ቦምብ በጊታር መያዛ ውስጥ ተደብቆ ከዌስት ባንክ ወደ እየሩሳሌም እንዲገባ ተደርጓል፡፡ አል-ታሚሚ እንደ ሙከራ እንዲሆን አስቀድማ በእየሩሳሌም በሚገኝ የሸቀጦች መደብር አነስተኛ ፈንጂ ማፈንዳቷን አምናለች፡፡
በ1995 ዓ.ም. አል-ታሚሚ በዚህ ጥቃት ውስጥ ስለመሳተፏ በእስራኤል ፍርድ ቤት ጥፋተኝነቷን አምና ቦምብ አፈንጂውን በማገዟ በእስራኤል የ16 አመታት እስር ተፈርዶባታል፡፡ ሆኖም ግን በጥቅምት 2003 ዓ.ም. በሀማስ እና በእስራኤል መካከል በነበረው የእስረኞች ልውውጥ ከእስር ተፈታለች፡፡ በመጋቢት 2009 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ ዲፓርትመንት በእርሷ ላይ የቀረበውን የወንጀክ ክስ በመክፈቱ በአል-ታሚሚ ላይ የእስር ትአዛዝ ወጥቷል፡፡ እንዲሁም ኤፍቢአይ አል-ታሚሚን እጅግ ተፈላጊ ወንጀሎች ዝርዝር ውስጥ አካቷታል፡፡