ወሮታ ለፍትሕ የሂዝባላህን የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎች ወደ ማዛባት የሚያመራ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
ናዚም ሰዒድ አሕመድ በሊባኖስ የሚገኝ ታዋቂ ገንዘብ አስተላላፊ ሲሆን፣ ለሂዝባላ ከፍተኛ ገንዘብ አቅራቢ ነው፡፡
አሕመድ ከሂዝባላ ከፍተኛ ረጂዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በ“ደም አልማዝ” ንግድ አማካኝነት ገንዘብ ያመነጫል፡፡ ሂዝባላ ለሽብር ቡድን የሚውል ገንዘብ ለማግኘት አሕመድን እና የእርሱን ኩባንያዎች ይጠቀማል፡፡ ከ2008 ዓ.ም. አጋማሽ አካባቢ ጀምሮ ለሒስባላ ገንዘብ ለማስተላለፍ ኩባንያዎቹን ተጠቅሟል፤ እንዲሁም ለሂዝባላ ዋና ጸሐፊ ሐሰን ነስረላህ በግል ገንዘብ ሰጥቷል፡፡ ከዚህም ሌላ “በደም አልማዝ” ሕገ ወጥ ዝውውር ከመሳተፉም ባሻገር ከዚህ ቀደም ለሂዝባላ ጥቅም ያስገኙ የንግድ ሥራዎች ቤልጂየም ውስጥ ሰርቷል፡፡
አሕመድ በዩናይትድ ስቴትስ የተጣለበትን ማዕቀብ ተጽዕኖ ለመቀነስ ከግል ገንዘቡ መካከል የተወሰነውን ከፍተኛ ዋጋ ባላቸው የሥነ ጥበብ ሥራዎች/ስዕሎች ቀይሮ ያስቀምጣል፡፡ አሕመድ በአስር ሚሊዮን የሚቆጠር ዋጋ የሚያወጡ ስዕሎች/ የሥነ ጥበብ ሥራ ውጤቶች አሉት፡፡ ከሥነ ጥበብ ሥራዎች ስብስቡ መካከል የፓብሎ ፒካሶ እና የአንዲ ዋርሆል ይገኙባቸዋል፤ እነርሱም በቤይሩት በሚገኘው የስዕል ጋለሪው እና የስዕል መደብር ውስጥ ለጉብኝት ቀርበዋል፡፡ በከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ እና ሕገወት ዝውውር አማካኝነት አሕመድ ንብረቶቹን ከሕጋዊ የግብር ከፋያ ለማሸሽ ሞክሯል፡፡ በሕገ-ወጥ መንገድ ያገኛቸውን ጥቅሞች ከሊባኖስ መንግሥት ለመደበቅ ሊባኖስ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ፈተናዎች ገጥመዋት እያለ ለሊባኖስ ሕዝብ እጅግ አስፈላጊ የሆነውን ግብር ሳይከፍል ቀርቷል፡፡
በታኅሳስ 03 ቀን 2012 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አሕመድን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፤ በዚህ መልክ ለመሰየሙ ምክንያት የሆነው ደግሞ ለሂዝቦላህ ወይም ሂዝቦላን ለመደገፍ በማለት የማቴሪያል፣ የገንዘብ ወይም የቴክኖሎጂ ድጋፍ በማድረግ ምክንያት ነው፡፡ በዚህም መልኩ በመሰየሙ ምክንያት ሌሎች ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአሕመድ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአሕምድ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡