የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ይፋዊ ዌብሳይት

ተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን (ቲቲፒ)

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን (ቲቲፒ) በ1999 ዓ.ም. የተመሠረተ የፓኪስታን እና አፍጋኒስታን ሽብርተኛ ድርጀት ነው፡፡ ዓላማውም በሽብር ድርጊቶች የፓኪስታንን መንግሥት ከኻይበር ፓኽቱንከዋ ክፍለ አገር (በይፋ በፌደራል መንግሥት የሚተዳደሩ የጎሳ አካባቢዎች ተብሎ የሚጠራ) ማስወጣት እና የሸሪዓ ሕግ አስተዳደርን መመሥረት ነው፡፡ ተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን ርዕዮተ ዓለማዊ ምሪት የሚያገኘው ከአል-ቃዒዳ ሲሆን፣ የአል-ቃዒዳ አካላት ደግሞ በአፍጋኒስታን እና ፓኪስታን ድንብር በተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታም ተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን የአል-ቃዒዳ የሽብር ኔትወርክ ተደራሽ እንዲሆንለት እና የአባላቱ የእንቅስቃሴ ሙያን እንዲቀስም አስችሎታል፡፡

ተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን (ቲቲፒ) ለበርካታ በፓኪስታን እና በዩናይትድ ስቴትስ ጥቅሞች ላይ ለተፈጸሙ የሽብር ድርጊቶች ኃላፊነት ወስዷል፤ ከእነዚህም መካከል በታኅሳስ 2001 ዓ.ም. በኾስት፣ አፍጋኒስታን የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ የተፈጸመው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት እንዲሁም በሚያዝያ 2002 ዓ.ም. በፔሻዋር፣ ፓኪስታን የተፈጸመው እና ስድስት የፓኪስታን ዜጎችን የገደለው በዩናይትድ ስቴትስ ቆንስላ ላይ የተፈጸመ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ይካተታሉ፡፡ ተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን በቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤናዚር ቡቶ ላይ በ1999 ዓ.ም. የተፈጸመው ግድያ ላይ ሳይሳተፍ አይቀርም ተብሎ ይጠረጠራል፡፡ ተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን በሚያዝያ 23 ቀን 2002 ዓ.ም. በኒው ዮርክ ከተማ ታይምስ አደባባይ በፈይሰል ሻሃዛድ የተሞከረው እና ያልተሳካው ፈንጂ የማፈንዳት ሙከራ መርቷል፣ አመቻችቷል፡፡

በነሐሴ 26 ቀን 2002 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን (ቲቲፒ)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት እንዲሁም ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን (ቲቲፒ) ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን (ቲቲፒ) ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ተህሪክ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን (ቲቲፒ) ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

SUBMIT A TIP

Do Your Part. Secure a Safer World.

There are many ways to submit information to Rewards for Justice.

You may choose from multiple platforms and contact us in numerous languages. To process your information efficiently, we ask you to state your information as succinctly as possible, provide your name, location, and preferred language, and upload all relevant files such as photographs, videos, and documents to support your information. An RFJ representative will soon contact you. Please be patient, as RFJ reads every tip we receive.

Please open your Signal app to submit a tip. The number is +1 202 702 7843

Please open your Line app to submit a tip. The number is +1 202 702 7843

Please open your Telegram app to submit a tip. The number is +1 202 702 7843

Please open your Viber app to submit a tip. The number is +1 202 702 7843

Please visit our Tor-based tips-reporting channel at: he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion

መረጃ ይስጡ

የበኩልዎን ያድርጉ

መረጃ ለማቅረብ በርካታ መንገዶች አሉ፡፡

ከተለያዩ ፕላትፎርሞች ሊመርጡ እና በተለያዩ ቋንቋዎች ሊያገኙን ይችላሉ፡፡ የእርስዎን መረጃ በውጤታማነት ለማካሄድ እንዲችሉ፣ የሚሰጡትን መረጃ በተቻለ መጠን እጥር፣ ምጥን ባለ መልኩ እንዲያቀርቡ እንጠይቅዎታለን፤ እንዲሁም ስምዎን ፣ የሚገኙበትን ቦታ፣ የሚመርጡትን ቋንቋ እና እንደ ፎቶግራፍ፣ ቪድዮ እና ሰነዶች ያሉ የእርስዎን መረጃዎች የሚደግፉ ማስረጃዎች አፕሎድ እንዲያደርጉ ልንጠይቅዎ እንችላለን፡፡ የወሮታ ለፍትሕ ወኪልም በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገኝዎታል፤ እባክዎን በትዕግስት ይጠብቁን፤ ወሮታ ለፍተሕ እያንዳንዱን መረጃ ያነብባል፡፡

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን ሲግናል ማመልከቻዎን ይክፈቱለ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን Line ማመልከቻዎን ይክፈቱለ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን የቴሌግራም አፕሊኬሽንዎን ይክፈቱ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

መረጃ ለማቅረብ እባክዎን የቫይበር አፕሊኬሽንዎን ይክፈቱ፡፡

ቁጥሩ የሚከተለው ነው፡- +1 202 702 7843

እባክዎን በቶር ላይ የተመሠረተ የመጃዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቻናላችንን በዚህ ያግኙ፡- he5dybnt7sr6cm32xt77pazmtm65flqy6irivtflruqfc5ep7eiodiad.onion

Skip to content