ወሮታ ለፍትሕ በጥር 07 ቀን 2011 ዓ.ም. በናይሮቢ ኬኒያ በዱሲት ዲ2 ሆቴል ላይ በአልሸባብ ሽብርተኞች ለደረሰው ጥቃት በኃላፊነት ስለሚጠየቀው መሐሙድ አብዲ አደን እና ሌላ ማንኛውም ሰው መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ወሮታ ይከፍላል፡፡ በጥር 07 ቀን 2019 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ፈንጂዎች፣ አውቶማቲክ መሣሪያ እና ቦምቦች የያዙ የአልሸባብ ታጣቂዎች መደብሮች፣ ቢሮዎች እና ሆቴል በያዘው ባለ ስድስት ፎቅ ዱሲት ዲ2 የንግድ ማዕከል ላይ ጥቃት ፈጸሙ፡፡ በዚህ ጥቃት የዩናትድ ስቴትስ ዜጎችን ጨምሮ ቢያንስ 21 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የአል-ቃዒዳ የሽብር ድርጅት ተባባሪ የሆነው አል-ሸባብ ሸሃዳ ዜና በሚል ስያሜ በሚታወቀው የዜና ኤጀንሲው አማካኝነት በመላው ጥቃት ወቅት ወቅታዊ መረጃዎች ያስተላልፍ ነበር፡፡ በሰጠውም ጋዜጣዊ መግለጫ ጥቃቱ የተፈጸመው በአል-ቃዒዳ መሪ በአይመን አልዘዋሂሪ በተሰጠ ትዕዛዝ መሠረት እንደሆነ ግለጾዋል፡፡
አደን፣ አንዱ የአልሸባብ መሪ ሲሆን፣ በጥር 2019 የተፈጸመውን ጥቃት ለማቀድ እገዛ አድርጓል፡፡ በጥቅምት 07 ቀን 2015 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህንን ግለሰብ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ (SDGT) በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡
አል-ሸባብ በኬኒያ፣ በሶማሊያ እና በአጎራባች አገራት የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን ጨምሮ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ተጠያቂ ነው፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ሸባብን በውጭ አገር የሚገኝ የሽብር ድርጅት እና ዓለም ዓቀፍ ልዩ ሽብርተኛ በማለት በመጋቢት 2000 መዝግቦታል፡፡ በሚያዝያ 2002፣ አል-ሸባብ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት የሶማሊያ ማዕቀቦች ኮሚቴ በውሳኔ ቁጥር 1844 (2008) አንቀጽ 8 ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ተሰይሟል፡፡