ወሮታ ለፍትሕ ስለ አሊ ሳዪድ ሙሀመድ ሙስጠፋ አል-ባክሪ በሌላ ስሙ አብድ አል-አዚዝ አል-ማስሪ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል- ባክሪ የአል-ቃዒዳ (ኤኪው) ሹራ ምክር ቤት አባል ነው፡፡ ይህ ምክር ቤት የቡድኑ ውሳኔ ሰጪ አካል ሲሆን ከአል-ቃዒዳ መሪዎች ሳዪፍ አል-አድል እና አይማን አል-ዛዋሂሪ ጋር የቅርብ ግንኙነት አላቸው፡፡ አል-ባክሪ የፈንጂዎች እና የኬሚካል ባለሙያ ነው፡፡
የአል-ቃዒዳ አባል ከመሆኑ በፊት አል-ባክሪ በአል-ዛዋሂሪ የሚመራው የግብፅ የእስላማዊ ጅሃድ ሽብርተኛ ቡድን አባል ነው፤ ይህ ግለሰብ በአፍጋኒስታን በሚገኙ አል-ቃዒዳ ካምፖች ለሰልጣኝ ሽብርተኞችን በፈንጂዎች እና በኬሚካል አጠቃቀም ላይ ስልጠና ይሰጥ ነበር፡፡ አል-ባክሪ በታኅሳስ 1993 ዓ.ም. የፓኪስታንን የተጓዦች አውሮፕላን ለመጥለፍ ሞክሯል፡፡ አሁንም የአል-ቃዒዳ ሽብርተኞችን እና ሌሎች አክራሪዎችን እያሰለጠነ ሊሆን ይችላል፡፡
አል-ባክሪ በኢራን ከቤተሰቡ ጋር ይኖራል፡፡
በመስከረም 23 ቀን 1998 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የየገንዘብ ሚኒስቴር አል-ባክሪን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ባክሪ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ባክሪ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ አል-ቃዒዳ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡