ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሲራጁዲን ሃቃኒ፣ በሌላ ስሙ ሰራጅ ሃቃኒ እና ኻሊፋ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሲራጁዲን በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት (ኤፍቲኦ) ተብሎ የተሰየመውን ሃቃኒ ኔትወርክ (ኤችኪውኤን) ይመራል፡፡ በእርሱ አመራር ስር ሃቃኒ ኔትወርክ (ኤችኪውኤን) በአፍጋኒስታን የዩናይትድ ስቴትስ እና ጥምር ኃይሎች፣ በአፍጋኒስታን መንግሥት እና በንጹሃን ዜጎች ላይ በርካታ ከፍተኛ እገታዎች እና ጥቃቶች አቅዷል፣ ፈጽሟል፡፡ በ2007 ዓ.ም. ሲራጁዲን የታሊባን ምክትል መሪ ሆኖ እንዲያገለግል በመሾሙ በኤችኪውኤን እና በታሊባን መካከል ላለው ትብብር ጠንካራ መሠረት ጥሏል፡፡
ከአሜሪካ የዜና ድርጅት ጋር በነበረው ቃለ መጠይቅ፣ ሲራጁዲን በጥር 05 ቀን 2000 ዓ.ም. በካቡል፣ አፍጋኒስታን በሰረና ሆቴል ላይ የተፈጸመውን ጥቃት እንዳቀደ አምኗል፤ በዚህ ጥቃት የአሜሪካ ዜጋ ቶር ዴቪድ ሄስላን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ሞተዋል፡፡ ሲራጁዲን በአፍጋኒስታን ፕሬዚደንት ሃሚድ ካርዛይ ላይ በሚያዝያ 2000 ዓ.ም. የተፈጸመውን የግድያ ሙከራ ማቀዱንም አምኗል፡፡
በመጋቢት 02 ቀን 2000 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲራጁዲን ሃቃኒን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሲራጁዲን ሃቃኒ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሲራጁዲን ሃቃኒ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ኤኪውኤን ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡