ወሮታ ለፍትሕ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተመዘገበው ሪቮሉሽነሪ ፒፕልስ ሊበሬሽን ፓርቲ/ግንባር (ዲኤችኬፒ/ሲ) ቁለፍ መሪ ስለሆነችው ሰኸር ደሚር ሴን፣ በሌላ ስሟ ሙነቨር ኮዝ ወይም አልባ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $3 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ይህ ቡድን በቱርክ ውስጥ በሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቀሞች ላይ ጥቃት ፈጽሟል፡፡
ሴን ዴቭሪሚሲ ሶል (ዴቭ ሶል) የተሰኘው ድርጅት አባል የሆነችው በ1972 ዓ.ም. ነበር፤ እስከ 1986 ዓ.ም. ድረስ አባል ሆናም ቆይታለች፡፡ በግሪክ የዲኤችኬፒ/ሲ ከፍተኛ አመራር ለመሆን ቻለች፤ በኤንስ የቡድኑ መሥሪያ ቤት ኃላፊ በመሆን አገልግላለች፡፡ ሴን የቡድኑ ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል ዲኤችኬፒ/ሲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ናት፡፡