ሪቮሉሽነሪ ፒፕልስ ሊበሬሽን ፓርቲ/ፍሮንት (ዲኤችኬፒ/ሲ) በ1970 ዓ.ም. በቱርክ ተመሠረተ፡፡ ዲኤችኬፒ/ሲ የማርክሲስት ሌኒኒስት ርዕዮተ ዓለምን የሚያቀነቅን እና ዩናይትድ ስቴትስን፣ ኔቶን እና የቱርክን መንግሥት የሚቃወም ድርጅት ነው፡፡ ይህ ቡድን ከ1980ዎቹ ጀምሮ በአሜሪካን ጥቅሞች ማለትም የአሜሪካን ሠራዊት እና የዲፕሎማሲ አካላት እና ተቋማት፣ የኔቶ ሠራተኞችን እና ፋሲሊቲዎች የጥቃት ዒላማ አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡፡ በየካቲት 2005 ዓ.ም. የዲኤችኬፒ/ሲ አባል በአንካራ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ አፈነዳ፡፡ ይህ ፍንዳታ አንድን ቱርካዊ የጥበቃ አባል ሲገድል፣ አንድ የቱርክ ጋዜጠኛ ደግሞ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶበታል፡፡ በመጋቢት 2005 ዓ.ም. ሦስት የቡድኑ አባላት ቦምብ እና ሪኬት ላውንቸሮች በመጠቀም በፍትሕ ሚኒቴር እና በአንካራ በሚገኝ የቱርክ የፍትሕ እና ልማት የፖለቲካ ፓርቲ ዋና መሥሪ ቤት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡፡
በመስከረም 28 ቀን 1990 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪቮሉሽነሪ ፒፕልስ ሊበሬሽን ፓርቲ/ፍሮንት (ዲኤችኬፒ/ሲ)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ በጥቅምት 21 ቀን 1994 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪቮሉሽነሪ ፒፕልስ ሊበሬሽን ፓርቲ/ፍሮንትን ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሪቮሉሽነሪ ፒፕልስ ሊበሬሽን ፓርቲ/ፍሮንት ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሪቮሉሽነሪ ፒፕልስ ሊበሬሽን ፓርቲ/ፍሮንትቲ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሪቮሉሽነሪ ፒፕልስ ሊበሬሽን ፓርቲ/ፍሮንት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡