ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሙሃመድ አሕመድ አል-ሙናዋር በሌላ ስሙ አብዳራህማን አል-ረሺድ ማንሱር እና አሽራፍ ናኢም ማንሱር መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ሙናዋር አቡ ኒዳል የተባለው የሽብርተኞች ድርጅት አባል ነው ይባላል፤ እርሱም በካራቺ በነሐሴ 30 ቀን 1978 ዓ.ም. በፓን አም በረራ 73 በተፈጸመው የአውሮፕላን ጠለፋ ላይ ለነበረው ተሳትፎ ይፈለጋል፡፡ 379 ተሳፋሪዎችን እና የበረራ ሠራተኞችን ለ16 ሰዓታት ያህል አግተው ካቆዩ በኋላ፣ አጋቾቹ በጭፍን ተኩስ ከፈቱ፤ በዚህም ሁለት አሜሪካዊያንን ጨምሮ ሃያ ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል፡፡
በጠለፋው ላይ ለነበረው ተሳትፎ አል-ሙናዋር በዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ግራንድ ጁሪ የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል ውሳኔ የተሰጠበት ሲሆን፣ በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተካቷል፡፡