ወሮታ ለፍትሕ ስለ መሐመድ ማካዊ ኢብራሂም መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ይህ ግለሰብ በታኅሳስ 22 ቀን 2000 ዓ.ም. በራሃማ፣ ካርቱም የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም ዓቀፍ ልማት ኤጀንሲ ሠራተኞች የነበሩትን ጆን ግራንቪል እና አብደልራህማን አባስ ራሃማን ለሞት የዳረገው ጥቃት መሪ ነበር፡፡ ማካዊ የዩናይትድ ስቴትስን፣ የምዕራቡን ዓለም እና የሱዳናዊያንን ጥቅም ለማጥቃት ሲያሴር የነበረው አል-ቃዒዳ በሁለቱ ናይሎች (አል ቃዒዳ ኢን ዘ ቱ ናይልስ) ተብሎ ከሚታወቀው ቡድን ጋር ግንኙነት ነበረው፡፡
ማካዊ በእነዚህ ግድያዎች ውስጥ ለነበረው ተሳትፎ ለነበረው ተሳትፎ በሱዳን ፍርድ ቤት ክስ ቀርቦበት፣ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ2001 ዓ.ም. የሞት ቅጣት ተላልፎበታል፡፡ ሆኖም ግን የሞት ቅጣቱ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት በሰኔ 03 ቀን 2002 ዓ.ም. ከእስር ቤት አምልጧል፡፡ አሁንም አልተገኘም፤ በሶማሊያ ይገኛል ተብሎ ይታመናል፡፡
በታኅሳስ 30 ቀን 2005 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማካዊን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የማካዊ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከካራቴ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡