ወሮታ ለፍትሕ የሂዝባላን የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎች ለማሰናከል የሚያስቸል መረጃ ለሚሰጥ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ መሀመድ ኢብራሂም ባዚ በቤልጂም፣ ሊባኖስ፣ ኢራቅ እና በበርካታ የምዕራብ አፍሪካ አገራት ውስጥ ወይም በእነርሱ በኩል የንግድ ዕንቅስቃሴዎች የሚያደርግ ቁልፍ የሂዝባላ ፋይናንስ አቅራቢ ነው፡፡ ባዚ ከንግድ እንቅስቃሴዎቹ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለማስገኘት ችሏል፡፡
ባዚ ግሎባል ትሬዲንግ ግሩፕ ኤንቪ፣ ዩሮ አፍሪካን ግሩፕ ሊሚትድ፣ አፍሪካ ሚድል ኢስት ኢንቬስትመንት ግሩፕ ሊሚትድ፣ አፍሪካ ሚድል ኢስት ኢንቬስትመንት ሆልዲንግ ኤስኤኤል፣ ፕሪሚየር ኢንቬስትመንት ግሩፕ ኤስኤኤል ኦፍሾር እና ካር ኤስኮርት ሰርቪስስ ኤስ.ኤ.ኤል የተባሉ ድርጅቶች ባለቤት ነው ወይም አነዚህን ኩባንያዎች ይቆጣጠራል፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ሁሉ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ማዕቀብ የተጣለባቸው እና ለሂዝባላ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያቀርቡ ናቸው፡፡
በግንቦት 09 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር መሐመድ ኢብራሂም ባዚን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የባዚ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከባዚ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡