ሃያት ታህሪር አል-ሻም (ኤችቲኤስ) የተመሠረተው በ2009 ዓ.ም. በአል-ኑስራህ ግንባር (ኤኤንኤፍ) እና በበርካታ ሌሎች ቡድኖች ውህደት አማካኝነት ነበር፡፡ ሃያት ታህሪር አል-ሻም በሶሪያም ሰሜን ምዕራብ አካባቢ የተወሰነውን ክፍል ይቆጣጠራል፤ ዓላማውም የአሳድን አገዛዝ መጣል እና በሱኒ ኢስላማዊ መንግሥት መተካት እና በሶሪያ ከአል-ቃዒዳ ተባባሪ ድርጅቶች መካከል አንዱ እንደመሆኑ መጠን የራሱን አጀንዳ ማራመድ ነው፡፡ ሃያት ታህሪር አል-ሻም ከሶሪያ ተቃዋሚዎች የተለየ አክራሪ ድርጅት ሲሆን፣ በአካባቢዊ አስተዳደር እና በውጭ አገራት ስለሚፈጸሙ እንቅስቃሴዎች በመዶለቱ ረገድ ልዩ ልዩ ተጽዕኖዎች ያደርጋል፡፡